በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቦንጋ ከተማ ጥራታቸው የተጠበቁ እና የዘር ምንጫቸው የታወቁ የአትክልት ዘሮች እና ሌሎች ኬሚካሎች ለኤግዚቢሽን ቀረበ

Spread the love

በኤግዚቢሽኑ በርካታ ካምፓኒዎች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ማርቆስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የተለያዩ አትክልት ዘሮች፣ ሚኢረጅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የጸረ አረምና ጸረ ተባይ ኬሚካል የኬምቴክስ የግብርና ምርቶች፣ ዋይዝ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ድርጅት የአትክልት ዘር፣ እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ ድርጅቶች ምርቶቻቸውን ለእይታ አቅርበዋል።

በኤግዚብሽኑ ምርቶቻቸውን ይዘው የቀረቡ የተለያዩ ድርጅቶች ለምርትና ምርታማነት ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው ምርቶችን በማስተዋወቅ በቀጣይ ለአርሶ አደሩ ለማቅረብ እንደሆነም ገልጸዋል።

በኤግዚቢሽኑ አግኝተን ያነጋገርናቸው የክልሉ ግብርና ቢሮ የሆርቲካልቸር ሰብሎች ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ገ/ሚካኤል ክልሉ በአትክልት እና በስራስር ሰብሎች በዓመት አራት አዝመራዎች የሚመረት አከባቢ ነው ብለዋል።

እነዚህም በበልግ፣በመኸር እንዲሁም በአንደኛ ዙር እና በሁለተኛ ዙር መስኖ ይለማሉ ያሉት አቶ ተስፋዬ በክልሉ ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንዲያግዝ የዘር አቅርቦት ችግር ለመፍታት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛልም ብለዋል።

በኤግዚቢሽኑ በርካታ የዘር አቅራብ ካምፓኒዎች የተሳተፉ ሲሆን ይህም የዘር አቅራቢዎች ጥራቱ የተጠበቀ እና ምንጫቸው የታወቁ ዘሮችን በማስተዋወቅ ቀጣይ ወደ አርሶ አደሩ ለማድረስ ምቹ መደላድል የሚፈጥር እንደሆነም አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል።

የክልልና የዞን ባለድርሻ አካላት በተለያዩ ድርጅቶች በኩል ለኤግዚቢሽን የቀረቡ ምርቶችን ተዘዋውረው ጎብኝቷል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *