በክልሉ ለግብርና ምርትና ምርታማነት ዕድገት አጋዥ የሆኑ የተለያየ አማራጮችን በተገቢው በመጠቀም የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ይሰራል-አቶ አሸናፊ ክንፉ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ግብርና ቢሮ የሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ የባለድርሻ አካላት የውይይት እና የግብርና ግብዓት ኤግዚቢሽን በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።

የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትልና የሆርቲካልቸር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አሸናፊ ክንፉ ክልሉ በተፈጥሮ ጸጋ የታደለ ሰፊ መልማት የሚችል መሬት፣ለግብርና ሥራ ምቹ ስነምህዳርና ውሃ አማራጮች ያለበት አከባቢ እንደሆነም ገልጸዋል።

እነዚህ በክልሉ የሚገኙ ለግብርና ምርትና ምርታማነት ዕድገት ምቹ የሆኑ ሰፊ አማራጮችን አሟጦ በመጠቀም የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ መሥራት ይጠበቅብናልም ብለዋል።

የግብርና ምርታማነት በዘላቂነት ለማሳደግ ከተለያዩ ባለድርሻ ተቋማትና አካላት ጋር ትስስር በማጠናከር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ያሉት አቶ አሸናፊ፤ SNV HORT LIFE 3 program ጋር በቅንጅት በተሰራው ሥራ ውጤቶች መመዝገባቸውን እና ይህም ቅንጅት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።

የግብርና ምርት ሲመረት የአርሶ አደር ጥቅም ብቻ ሳይሆን መላው የሀገሪቱ ህዝብ የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ እና የሀገር የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ ስለሆነ በክልሉ ለግብርና ምርት ዕድገት ምቹ የሆኑ የተለያዩ አማራጮችን በተገቢው መጠቀም ያስፈልጋልም ብለዋል።

በውይይት መድረኩ የሆርቲካልቸር ሰብሎች የእስካሁን አፈጻጸም ሪፖርት የግብርና ቢሮ የሆርቲካልቸር ሰብሎች ልማትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ገ/ሚካኤል እያቀረበ ይገኛል።

ከሚቀርበው ሰነድ መነሻ እስካሁን በጥንካሬ የተመዘገቡ ውጤቶችን ማጠናከር እና ጉድሌቶች ማረም በሚያስችል ጉዳዮች ዙሪያ ባለድርሻ አካላት ውይይት ይደረጋል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *