የክልሉ ገቢዎች ቢሮ በሩብ ዓመቱ ከ3.7 ቢሊዮን ብር በላይ ሰበሰበ

Spread the love

የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት አሰግድ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ ከ3.7 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታውቀው ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ1.87 ቢሊዮን ብር ጭማሪ ማሳየቱን ገልጸዋል።

ቢሮው አፈጻጸሙን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በገመገመበት ወቅት፣ ምንም እንኳ ከተያዘው አጠቃላይ ዕቅድ አንጻር መጠነኛ ክፍተት ቢኖርም፣ የተመዘገበው የገቢ መጠንና ዕድገት በራሱ ትልቅ ስኬት መሆኑን ኃላፊዋ ገልጸዋል።

በማህደር ምርመራ ዘርፍ 878 ሺህ ብር ገደማ ለማግኘት ታቅዶ፣ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ መቻሉ የተገለፀ ሲሆን

338 ግብር ከፋዮችን ከደረጃ ‘ለ’ ወደ ደረጃ ‘ሀ’ ለማሳደግ ታቅዶ፣ ከዕቅድ በላይ በመሥራት 356 ግብር ከፋዮችን ማሸጋገር መቻሉም በሪፖርቱ ተመላክቷል።

ዘመናዊውን የሲግታስ (SIGTAS) ቴክኖሎጂ በ66 የታክስ ማዕከላት ሥራ ላይ በማዋል በሺዎች የሚቆጠሩ የሰነድና የአሳስመንት ሥራዎችን በማከናወን የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ግልጽ ማድረግ ተችሏል ተብሏል።

ከ17,000 በላይ ለሚሆኑ ነባር እና ከ2,000 በላይ ለሆኑ አዲስ ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመስጠት የታክስ ሥርዓቱን የተማከለና ፍትሐዊ ለማድረግ ሰፊ ጥረት መደረጉም ተጠቁሟል።

ይህ ውጤት መላው የቢሮው ሠራተኞችና አመራሮች ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት የተገኘ ነው ያሉት ወ/ሮ ህይወት በቀጣዩ ሩብ ዓመት ከዚህ የተሻለ በመሥራት የህዝቡን የልማት ጥያቄ የሚመልስ ገቢ አሟጠን መሰብሰብ አለብን” ሲሉ የወደፊቱን አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

የተቋሙ አመራሮችም የታክስ ማጭበርበርን መከላከል፣ የአገልግሎት አሰጣጥን ማዘመን እና ግብር ከፋዩ ከመሥሪያ ቤቱ ጋር ያለውን መተማመን ማሳደግ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

መረጃው የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *