በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሠላማዊ የመማር፣ ማስተማር ስራው እንዲቀጥል የባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ ነው:- አቶ ነጋ አበራ

Spread the love

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሠላማዊ የመማር፣ ማስተማር ስራ እንዲቀጥል በማድረግ ብቁ ዜጋን ለማፍራት ያለመ የባለድርሻ አካላት ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አቶ ነጋ አበራ፥ የብልጽግና ፓርቲ በ2018 በጀት ዓመት ከተስፋ ወደ ሚጨበጥ ብረሃን ለመሻገር ያያዘውን ራዕይ እውን ለማድረግ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ ምሁራን ሚና ከፍተኛ መኾኑን ተናግረዋል።

ፓርቲው በሀገሪቱ እውነተኛ የዴሞክራሲ ስርዓት እውን እንዲኾን በትኩረት እየተንቀሳቀሰ መኾኑን የጠቆሙት አቶ ነጋ፥ በዚህም በቀጣይ ትላልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ መሸከም የሚችል አደረጃጀት ለመፈጠር እየተሰራ እንደሆነም አንስተዋል።

በቀጣይ ከሚኖሩ ሀገራዊ አጀንዳዎች ጋር በተያያዘ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያለው የመማር፣ ማስተማር ተግባር ያለ ማንም የፖለቲካ ጠልቃ ገብነት እንዲቀጥል የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ኃላፊነት እንደተጣለባቸውም አቶ ነጋ ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ በከተሞች ህዝብን ለምሬት የሚዳርጉ ጉዳዮችን ለይተው ለመፍታት በትኩረት እየሰራ መኾኑን የገለጹት አቶ ነጋ በመፍትሔ ላይ የምሁራን ሀሳብ ትልቅ ግብዓት እነደሆነ ተናግረዋል።

በክልሉ ውስጥ ሆነ ከክልሉ ውጪ በሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ያለው ተሞክሮዎች በማጋራት እና መረጃ በመለዋወጥ በቀጣይ በቅንጅት ለመስራት መድረጉ የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለውም አቶ ነጋ ተናግረዋል።

ምሁራንን በምክንያታዊ፣ ሚዛናዊ፣ እንዲሁም ደሞክራሲያዊ እና ነጻ የፖለቲካ ትግል ላይ በማሳተፍ ለሀገር አውንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያረክቱ ማድረግ እንደሚገባም ነው በክልሉ ብልጽግና ፓርቲ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክትትል ዳይሬክተር አቶ ዘላለም ለገሰ የገለጹት።

አቶ ዘላለም አክለው፥ ዩኒቨርስቲዎች ከተቋቋመበት ዓላማ አንጻር የመማር ማስተማር ተግባር ምቹ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ወሳኝ መኾኑን ጠቁመዋል።

ምሁራን ለሀገራዊ ተልዕኮ መሳካት የሚጫወቱትን ሚና እንዲያጎለብቱ ምቹ ሁኔታዎችን መፈጠር እንደሚገባ ያስገነዘቡት አት ዘላለም መድረኩ ለቀጣይ ሀገራዊ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ እንደሆነ ገልጸዋል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *