

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ እየሰጡ ነው።
ማብራሪያ ከሰጡባቸው ጉዳዮች ውስጥ መንግሥት ዳንጎቴ ከተባለ የውጭ ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያለማው የማዳበሪያ ፋብሪካ አንዱ ነው።
ፋብሪካው በዓመት 30 ሚሊዮን ኩንታል የዩሪያ ማዳበሪያ የማምረት አቅም እንዳለውም ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ ማዳበሪያን ከማምረት ባለፈ የሚመረተው ማዳበሪያ የአካባቢውን አፈር፣ የምርቱን አይነት እና ምጥጥኑን መሠረት ያደረገ እንዲሆን እየተሠራ መኾኑንም አብራርተዋል።
እያንዳንዱ የማዳበሪያ ምርት ባርኮድ ተሠጥቶት እና መዳረሻው ታውቆ እንዲሠራጭም ትኩረት ተደርጓል ብለዋል።
ማዳበሪያን በረከሰ ዋጋ አርሶ አደሩ ድረስ ማድረስ ሌላኛው ትኩረት እንደኾነም ገልጸዋል።
ከማዳበሪያ ማምረት ባለፈ 1ሺህ ሜጋ ዋት ኀይል ማመንጨት፣ የነዳጅ ማጣሪያን (ሪፋይነሪ) ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶችን ለማጠናቀቅ 10 ቢሊዮን ዶላር በጀት መመደቡን ገልጸዋል።
