

ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ጥረት ፈፅሞ ሊሳካ እንደማይችል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሰላም እና ፀጥታን በሚመለከት ለፓርላማው በሰጡት ማብራሪያ፣ የኢትዮጵያን ዕድገት የማይሹ ሀገራት በጦርነት እንደማያሸንፉን ስለሚያውቁ ያላቸው ምርጫ ባንዳዎችን መላክ ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያን በቅጡ ያላወቁ የውስጥ ባንዳዎች ደግሞ ከጠላት ጋር በማበር ዓላማቸውን የሚያሳኩ እንደሚመስላቸው ጠቁመው፣ ይህ ፈጽሞ ሊሳካ አይችልም ብለዋል።
ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያስፈልገው ብቻው መንገድ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር እንደሆነ እና መንግሥት ችግሮች አሉኝ የሚሉ አካላት ጋር ቁጭ ብሎ በመነጋገር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት አሁንም ክፍት መሆኑን በግልጽ አስቀምጠዋል።
