




በምዕራብ ኦሞ ዞን በመኤኒት ሻሻ ወረዳ ሰልጠና እየወሰዱ ያሉት የሚሊሻ አባላት የክልሉ የዞን የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተው ምልከታ አድርጓል ።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የክልሉ ሠላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ሃብታሙ እንደተናገሩት ሠላም የሁላችንም በመሆኑ በጋራ ተቀናጅተው መስራት አለብን ብልዋል።
የሚላሻ አባላት ዘላቂ የሆነ ሠላም ለማምጣት ተግተን በሠላም ሥራዎች ላይ ግንባር ቀደም ሚና መያዝ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
ህብረተሰቡ በቅርበት ለማገልገል ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸው እና ከህብረተሰቡ የሚመረጥ በስነምግባር የተመሰከረላቸው የአካባቢው ሠላም ማስጠበቅ በማጽናት የሚችል እና የተመለመለ መሆኑ ገልጸዋል።
የህዝብን ሰባዊ ክብራቸውን ጠብቆ ለማስቀጠል ወንጀለኞች ለህግ ለማክበር ሠላም ለማስጠበቅ ብቁ መሆን ይጠበቃል ብልዋል።
የህዝብን ሠላም እና ደህንነት ሲባል የመሳሪያ አያያዝ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የስነምግባር ስልጠናው
በአንድ ክስተት እና በአንድ ግለሰብ ጥፋት በርካታ ሞቶች መፈናቅሎች እንዲከሰቱ የሚያደርጉት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ማስቆም መቅረፍ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የክልሉ የሚሊሻ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለሙ ከስኩ በበኩላቸው የህዝብን የሠላም እና ደህንነት ሥራዎች የልማት ሥራዎች ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሰልጣኝ የሚሊሻ አባላት ሚናቸውን ከፍተኛ መሆኑ ገልጸዋል።
በየትኛውም አካባቢ የተለያዩ የእርስ በእርስ ግጭት ልከስት ይችላሉ በዛው የሰለጠናችሁ አባላት ከህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት ወንጀለኞች ለህግ ማቅረብ ይጠበቃል ብልዋል።
የመንግስት እና የፓርቲ ሥራዎች በዉጤት እንዲታጀብ ሰዉ በሠላም ወጥተው በሠላም እንዲገባ የአካባቢው ሠላም ማስጠበቅ የሁላችንም ሃላፊነት መሆኑ ተናግሯል።
የመኤኒት ሻሻ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደሳለኝ ዳዊት እንደተናገሩት የማህበረሠቡ ደህንነት ለመጠበቅ በወረዳ ከሁሉም ቀበሌዎች የተወጣጡ ከ116 በላይ የሚሊሻ አባላት ስልጠናው እየወሰዱ መሆናቸው ተናግሯል።
ስልጠናው ከቲኦሪ ባለፈው በዋናነት ተግባር ላይ መሰረት ያደረገ መሆኑን የተናገሩት አቶ ደሳለኝ የወረዳ ሰላም በዘላቂነት ለማስፈን የሰላም አስከባሪ የሚሊሻ አባላት ስልጠናው መስጠት አስፈላጊ መሆኑ አስገንዝበዋል።
የዞኑ ሠላም እና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ አቶ ባህሩ ቡርጂ እንደተናገሩት የሠላም ሥራዎች በተለይም የእርስ በእርስ ግጭት ለመፍታት መንግስት ትልቁ ሃላፊነት የጣለው በሚሊሻ መዋቅ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብልዋል።
በስነምግባር በአመለካከት እና በሌሎች ላይ የታነፀ አባላት እንዲኖር ስልጠና ይሰጣል ነው ያሉት ሲል የዞኑ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።
