




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአስተዳደር ዘርፍ የብልጽግና ህብረት የ2018 የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የአባለት ኮንፈረንስ ተካሂዷል።
የህብረቱ ሰብሳቢ አቶ ሳምሶን መለሰ እንደገለጹት የህብረቱ ዓባላት ፓርቲው ያነገባቸውን ተልዕኮዎቹን ከግብ ለማድረስ እያደረገ ያለው የተቀናጀ ጥረት አበረታች ለውጦችን ማስመዝገብ ችሏል።
2018 ዓም የህብረቱ አባላቱም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ዘመን ለማጽናት በፓርቲው የአሰራር ስርዓት መሠረት ብርቱ ውይይት በማካሄድ ተጭበጭ ለውጦችን እያስመዘገበ ይገኛል።
ቀደም ሲል የአመራርና የአባላት የግምገማና ምዘና መድረክ የፓርቲና የመንግስትን ተልዕኮን በብቃት ለመፈፀም የሚያስችል፤ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አቅም የሚፈጥር እንደሆነ የገለጹት አቶ ሳምሶን ለዚሁ ስኬትም በህብረቱ የሚደረጉት ውይይቶች ሚናቸው ከፍተኛ እንደነበር ጠቁመዋል።
ህብረቱ እስካሁን የገኙ ውጤቶችና ስኬቶችን እንደመስፈንጠሪያ አቅም በመጠቀም የፓርቲውን ደርብ ተልዕኮዎቹን በላቀ ብቃት ለማሳካት ከምንም ጊዜ በላይ ርብርብ ማድረግ ይጠበቃል ሲሉ አቶ ሳምሶን አስገንዝበዋል ።
በአመለካከት፣ በአስተሳሰብበ እና በስነ ምግባር አርአያነት እሳቤን የተላበሰ አባላትን ቁጥር ማሰደግ ይገባል ነው ያሉት።
አባላቱ የድህረ እውነት ዘመንን በውል በመገንዘብ የሚነሱ አሉባልታዎችንና ሀሰተኛ መረጃዎቹን በተደራጀ መልኩ መመከት እንዳለበትም ገልጸዋል።
