የመገጭ ግድብ የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር)

Spread the love

የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክት የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ÷ በጎንደር በነበረን ጉብኝት የመገጭ የመስኖ ልማት ፕሮጀክትን የሥራ ሁኔታ ገምግመናል ብለዋል።

ፕሮጀክቱ 870 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ÷ ሥራው ሲጠናቀቅ 17 ሺህ ሔክታር በመስኖ አቅርቦት ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስረድተዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ቁልፍ የሆነው የወንዝ ቅልበሳ ሥራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቅቋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)÷ ቀሪ ሥራዎችም በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተካሄዱ እንደሚገኙ ጠቅሰዋል።

የመገጭ መስኖ ልማት ፕሮጀክት በሚጠናቀቅበት ወቅት የአካባቢውን የግብርና ምርታማነት የሚያሳድግ ይሆናል ሲሉም አመልክተዋል ሲል ኤፍኤም ሲ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *