የሺሺንዳ – ቴፒ የአስፓልት መንገድ ግንባታ በሱር ኮንስትራክሽን ዳግም ተጀመረ

Spread the love

የሺሺንዳ እና ቴፒ ከተሞችን የሚያገናኘው የአስፓልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት፣ ከበርካታ የህዝብ ጥያቄዎች እና ከአንድ ዓመት በላይ ከዘለቀ መቆም በኋላ በአገር በቀል ድርጅት በሆነው ሱር ኮንስትራክሽን ዳግም ወደ ሥራ ተመልሷል። መንገዱን ቀደም ሲል የያዘው የውጭ ተቋራጭ CRCC በአሰራር ጉድለት እና በከፍተኛ መዘግየት ውሉ ተሰርዟል።

የቢጣ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን እንደገለጸው፣ የውጭው ተቋራጭ CRCC መንገዱን በአራት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ውል የገባ ቢሆንም፣ በሰባት ዓመታት ውስጥ ከአፈር ስራ የዘለለ ጉልህ ተግባር አለማከናወኑን መንግስት አረጋግጧል። በውጤቱም፣ መንግስት በህዝብ ላይ የደረሰውን የልማት ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት የCRCCን ውል ሰርዞ፣ ፕሮጀክቱን በአዲስ ጨረታ ለሱር ኮንስትራክሽን አስረክቧል።

መንገዱን የተረከበው አገር በቀል ኮንስትራክሽን ድርጅት ሱር ኮንስትራክሽን ጊዜ ሳያባክን ስራ መጀመሩ ተገልጿል።

መንገዱ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የህብረተሰቡ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን በመጥቀስ፣ የአካባቢው ነዋሪዎች በተለመደው ጨዋነት ለሱር ኮንስትራክሽን አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪውን አስተላልፏል።

በሺሺንዳ እና ቴፒ አካባቢ ለሚገኙ ነዋሪዎች የልማትና ትስስር አዲስ ምዕራፍ እንደሚከፍት ይጠበቃል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *