34ኛው ሀገር አቀፍ የትምህርት ጉባዔ ዛሬ በአዳማ ከተማ ተጀመረ

Spread the love

”ፍትሃዊና ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል በተጀመረው ጉባዔ የ2017 የትምህርት ልማት ዘርፍ አፈጻጸም ይገመገማል።

‎ጉባዌው በ2018 የትምህርት ዘመን እቅድ ላይ ውይይት በማድረግ ለተሻለ አፈጻጸም የሚያግዙ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል።

‎በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ እየተካሄደ በሚገኘው ሀገር አቀፍ ጉባዔ የኢፌዲሪ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

‎በተጨማሪም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት ሥራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ፣የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፣የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎችና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶችና አጋሮች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *