የሸኮ ወረዳ ቡና አምራች አርሶአደሮች ለቡናቸዉ ጥራት መጠበቅ የአካባቢው ደን አስተዋጽኦው ወሳኝ መሆኑን ተናገሩ።

Spread the love

የሸኮ ወረዳ አሰተዳደርም ከ36ሺ በላይሄክታር ቡና በደን የተሸፈነ መሆኑን ገልጿዋል ።

በቤንች ሸኮ ዞን የሸኮ ወረዳ ቡና አምራች አርሶአደሮች ቡና እና ደን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው ብሏል።

አቶ ሼንቸብ ጄቢ አቶ ሳሙኤል ደቹ እና አቶ ዳጩ ዚቲ በሸኮ ወርዳ ቡና አምራች አርሶአደሮች ሲሆኑ የሸኮ ቡናን ልዩ የሚያደርገው ቡናው እና ጫካው ከጥንት ጀምሮ ቁርኝታቸዉ እጅ እና ጓንት ነው ብለዋል።

አሁን ላይ ደኑን ይበልጥ በመንከባከብ ቡናችንን በጥራት በማምረት ለውጥ እያመጡ እንደሚገኙም ገልፀዋል ።

አርሶአደሮችም አክለው ቡናን በጥራት በማምረታቸው ተጠቃሚ ከመሆንም አልፎ በተለያዩ ኢንቨስትመንት ስራዎች በመሳተፍ እንደሚገኙም ገልፀዋል ።

የወረዳ ቡናና ሻይ ቅመማ ቅመም ልማት ጥበቃ ባለሙያ አቶ አለማየሁ ካሳ በበኩላቸው በወረዳው ያለውን የቡና ሽፋን አብዛኛው በደን የተሸፈነ መሆኑን ገልፀው ለአምራች አርሶአደሮች ሙያዊ ድጋፍ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል ።

የሸኮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሪ ጉርሙ የሸኮ ማህበረሰብ ጫካን መንከባከብ ከጥንት አባቶቻችን የመጣ ታሪካዊ ቅርስ መሆኑን ተናግረዋል ።

አስተዳዳሪው አክለው በወረዳው ከ 36ሺ ሄክታር በላይ የጫካ ቡና ማህበረሰቡ ደንን በመንከባከብ እያለሙ እንዳሉ አንስተው መላው አምራች አርሶአደሮች ከአባቶቻችን የወረስነው ትልቁ ሀላፊነታችን በመወጣት ደንን የመንከባከብ ባህላችን ለመጪው ትውልድ ማስረከብ ይኖርብናል ሲሉ ተናግረዋል ሲል የዘገበዉ ቤንች ሸኮ ቴቪ ነዉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *