የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾና የኢፌዲሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ሀዋሳ ከተማ ገቡ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾና የኢፌዲሪ ገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ በነገው ዕለት በሲዳማ ክልል “ህብረብሔራዊ ወንድማማችነት እና እህትማማችነት ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል የሚካሄደውን ህዝባዊ የውይይት መድረክ ለመምራት ሀዋሳ ከተማ ገብተዋል።

እንግዶቹ ሀዋሳ አለም አቀፍ አየር ማረፍያ ሲደርሱ የሲዳማ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አስፋው ጎኔሶ እና የክልሉ የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የፌስቡክ ገፅ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *