
በክልሉ የጤና አገልግሎት ያልታቋረጠ እያደ የሚመጣ የአገልግሎት ዘርፍ በመሆኑ ለማህረሰቡ መድኃኒት በጤና ተቋማት እና ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎች ለማቅረብ ትኩረት ተሰጥቷል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳዳሮች አንድ ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲ እንዲኖር በተቀመጠው ክልላዊ አቅጣጫ መሠረት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
ቢሮው በክልሉ ባሉ ከተማ አስተዳደሮች ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎችን በመገንባት ወደ ሥራ ማስገባት ለህብረተሰቡ የህክምና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ ይገኛል።
በዛሬው ቆይታ ከእኛ ጋር እንግዳ! ዝግጅታችን አጠቃላይ ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲ አገልግሎት በሚመለከት የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከክልሉ ጤና ቢሮ የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ከአቶ ምትኩ ታመነ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
”ቆይታ ከእኛ ጋር እንግዳ ዝግጅት”ከቢሮ የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ጋር የተደረገው አጠቃላይ ዝግጅት እንደሚከተለው ቀርበዋል
መልካም ንባብ!
መ/ኮ፦ በቅድሚያ ለቃለ ምልልሱ ፍቃደኛ ስለሆኑ እያመሰገንን፤ እንተዋወቅ ስምና ኃላፊነትዎን ቢገልጹልን?
እንግዳችን፦ እኔም አመሰግናለሁ ቆይታ ከእኛ ጋር እንግዳችሁ ስላደረጋችሁኝ! ስሜ አቶ ምትኩ ታመነ የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትልና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ፡፡
መንግሥት ኮሙኒኬሽን፦ በክልሉ ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎችን በማስፋፋት ለህብረተሰቡ የህክምና አገልግሎት በተሻለ ተደራሽ ለማድረግ እንዴት እየተሰራ ይገኛል፡፡
አቶ ታመነ፦በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶችን በመክፈት የህብረተሰቡን የመድኃኒት ፍላጎት ለማሟላት እየሰራ ይገኛል። ለዚህም በሁሉም ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳዳሮች ብያንስ አንድ ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲ እንዲኖር ሰፊ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ነው፡፡
መንግሥት ኮሙኒኬሽን፦ ምንያህል ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎች አሉ?
በክልላችን ባሉ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች 18 ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎችን በመገንባት ወደ ሥራ ማስገባት ተችሏል፡፡
መ/ኮ፦ ቢሮው ለነዚህ ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎችን እያደረገ ያለው ድጋፍ ካለ?
አቶ ታመነ፦ ሁሉም ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎች እንደ አዲስ ሥራ ስጀምሩ የክልሉ ጤና ቢሮ እስከ አንድ ሚሊየን ብር የሚጠጋ የመድኃኒት ብድር ከመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡
ከዚህ በፊት በጤና ተቋማት ከማህረሰቡ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ ሲነሳ የነበረው የህክምና መድኃኒት እጠረት የሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎች ተገንብተው አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በእጅጉ ቀርፏል፡፡
ነዋሪዎችም ከሞዴል የማህበረሰብ መድኃኒት ቤት በተመጣጣኝ ዋጋ አገልግሎት እያገኙ ነው፡፡
በክልሉ ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ሞዴል የማህበረሰብ መድኃኒት መደብር ማህበረሰቡን ከተጋነነ ወጪ እንደታደጋቸው ይገኛል፡፡
በአገልግሎቱ ነዋሪዎች ደስተኛ እያደረገ መሆኑና ከሞዴል ማህበረሰብ መድኃኒት ቤት የተለያዩ መድሃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበም ይገኛል።
መንግሥት ኮሙኒኬሽን፦ በጤና ተቋማት እና ሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎች የመድኃኒት አቅርቦት ቀጣይነት እንዲኖረው ቢሮው እንዴት እየሰራ ነው?
እንደ ክልል የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ በጀት ወደ ጤና ተቋማት ወርዷል ይህም አንደኛውን የመድኃኒት አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ ከተሰሩ ተግባራት ተጠቃሽ ነው፡፡
መ/ኮ፦ የሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎች ቁጥር ለማሳደግ ምን እየተሰራ ነው?
አቶ ታመነ፦ በክልሉ አሁን ተጨማሪ 4 በግንባታ ላይ እንደሚገኙና ይህም ሲጠናቀቀቅ የሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎች ቁጥር ወደ 22 ከፍ ያደርገዋል፡፡
መ/ኮ ማህበረሰቡ በመንግሥት ጤና ተቋማት እና የሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎች መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ እየገዛ ተጠቀሚ እንዲሆን የሚያስተላልፉት መልዕክት ካለ?
አቶ ምትኩ ታመነ፦ የጤና አገልግሎት ያልታቋረጠ እያደ የሚመጣ የአገልግሎት ዘርፍ በመሆኑ ለማህረሰቡ መድኃኒት ለጤና ተቋማት እና የሞዴል ማህበረሰብ ፋርማሲዎች እየቀረበ መሆኑንና ከነዚህ ተቋማት መድኃኒቶችን የመግዛት ባህል እንዲኖር ጥሪዬን አቀርባለሁ ፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
