በክልሉ የሲኦሲ(COC) እና ፈተና ማረምያ ፖርታል ማሽን ለምቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

Spread the love

ሪፖርታዥ

በክልሉ የሲኦሲ(COC) እና ፈተና ማረምያ ፖርታል ማሽን ለምቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

በአለም ላይ በየጊዜው አዳዲስ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ስራዎች ብቅ ብቅ ማለት ከጀመሩ ሰነባብቷል፡፡ ይህንን ተከትሎ  በቀጣይም በኢትዮጵያ ሀገራዊ ብልጽግናን ያረጋግጣል ተብሎ ከተለዩት ዘርፍ አንዱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ነው፡፡ለዚህም ሀገራችን ኢትዮጵያ አለም በቴክኖሎጂ የደረሰበትን ደረጃ በመገንዘብ የቴክኖሎጂ ዲጂታላይዘሽን ማዕቀፍ ውስጥ በማስገባት ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በቅንጅት  በመስራት ላይ  ትገኛለች፡፡

በዚህም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 እውን ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው፡፡የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም ይህንን የቴክኖሎጂ አብዮት ለመቀላቀል ከክልሉ ምስረታ ጀምሮ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሰፊ ስራ እየተሰራም ይገኛል፡፡

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የቴክኖሎጂ ዘርፍ ኃላፊ ወ/ሮ ቤቴሌሄም ዳንኤል እንደ ተቋም በቴክኖሎጂውና በዲጅታል ዘርፉ  ዓለም የደረሰበትን ደረጃ በሀገራችን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ አጠቃላይ ተግባራትን ዲጅታላይዝድ በማድረግ ለህብረተሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከሶፍት ዌር ድረገጽ ልማት አኳያ በርካታ አዳዲስ ሶፍት ዌር ድረገጽ አልምተን ወደ ስራ አስገብተናል ያሉት ወ/ሮ ቤቴሌሄም ክልሉ ከተቋቋመ ወዲህ ሁለት ሶፍት ዌር ድረገጽ በማልማት ወደ ስራ መገባቱን ጠቅሰው በዚህም በርካታ የሶፍትዌር እና ሃርድ ዌር ጥገና ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የዲጂታል ቴክኖሎጂን ተደራሽ ለማድረግ በክልሉ ሲስታም ፖርታሎችን በቢሮው ባለሙያዎች አልምቶ ወደ ስራ አስገብተዋል፡፡በክልሉ የሲኦሲና ሌሎች ፈተና ማረምያ ፖርታል ማሽን በማልማት ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል ያሉት ወ/ሮ ቤቴሌሄም እንደ አውሮፓ ዘመን አቆጣጠር በ2025 አብዛኛው ተግባራት ከወረቀት ነፃ ሙሉ በሙሉ በዲጅታል ቴክኖሎጂ  እንዲተገበሩ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሆነና ይህን ለማሳካትም ቢሮው እየሰራ መሆኑን ወ/ሮ ቤቴሌሄም ዳንኤል ገልፀዋል።  

ከወረቀት የጸዳ ክልልን ለመፍጠር ዶክመንት ሼሪንግ ፖርታል ለምቷል ብለዋል፡፡ ይህ ዶክመንት ሼሪንግ ፖርታል ማልማት በክልሉ የሚሰሩ ስራዎች ከወረቀት በፃዳ መልኩ ለማከናወን ያስችላል፡፡ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለመናኸሪያ አገልግሎት የሚውል የመናኸሪያ አውቶሜሽን ማሽን ወደ ስራ አስገብተን በዚህም ውጤታማ ተግባር እያከናወነን እንገኛለን ነው ያሉት፡፡

ይህንንም ስራ አጠናከረን እንቀጥላለን ያሉት ኃላፊዋ መሠረታዊ የኮምፒውተር ዕውቀትና ክህሎት ጋር በተያያዙ የሚፈጠሩ ችግሮችን በመፍታትና ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር ባለሙያዎች በቀላሉ በማለመድ በተቋማቸው በኮምፒውተር በመታገዝ ቀልጣፋና ወቅታዊ የሆነ ተልዕኮ በብቃት ለመፈጸም ሚናቸውን ከፍ እንዲያደርግ በቢሮው ደረጃ  የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎች በተገቢው ሁኔታና እየተሰጠ መሆኑን  ጠቁመዋል።

በክልሉ የቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት በቅርቡ እንደሚጀመር  ዘርፍ ኃላፊዋ አስታውቀዋል፡፡

ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከክልሉ መንግስት ጋር በትብብር የተገጠሙ መሆናቸውም ገልፀዋል ።

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የብዝሃ ማዕከላት አደረጃጀት ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ ሁለት ዓመታትን አስቆጥሯል።

የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለማህበረሰቡ አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የገለጹት ኃላፊዋ በክልሉ ሁሉም ከተሞች የተሳለጠ የቪዲዮ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የመግጠም ስራ መጠናቀቁን ተናግረዋል።

የክልሉ መንግስት ዜጎች ያለእንግልት ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት እንዲደራጁ ከፍተኛ ጥረት መደረጉንም ጨምረው ገልጸዋል።

ለቪዲዮ ኮንፈረንስ አገልግሎት የሚውሉ የቴሌቪዥን ስክሪኖችን በመግዛትና በስድስት ከተሞች የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል የመግጠም ስራዎች የተጠናቀቀ እና በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት መስጠት የሚጀመር  እንደሆነም ገልጸዋል።

በክልሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራዎች በተማሪዎች እየተዘጋጀ መቆየቱን የጠቀሱት በዚህም የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሽግግር ሂደትን የሚያሳልጥ ስራ ተሰርቷል ያሉት በቅርቡ በተማሪዎች የተሰሩ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስራ ውድድር ለማካሄድ የፈጠራ ስራ ኤግዝብሽን እንደሚዘጋጅም አመልክተዋል፡፡

በቀጣይ ክልላዊ የሆነ መረጃ ማስቀመጫ ዳታ ማዕከል ለመገንባት ዕቅድ ተይዞ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት  ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

One thought on “በክልሉ የሲኦሲ(COC) እና ፈተና ማረምያ ፖርታል ማሽን ለምቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *