ኢትዮጵያ በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በትምህርት ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ድሎች ታንጸባርቃለች::

Spread the love

ኢትዮጵያ በ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ በትምህርት ዘርፍ ያስመዘገበቻቸውን ድሎች እንደምታንጸባርቅ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

በጉባኤው ላይ ከአባል ሀገራቱ መሪዎች በተጨማሪ የስድስት ሀገራት መሪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተመላክቷል።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥቷል።

መግለጫውን የሰጡት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ፤ በጉባኤው 49 ሀገራት እንደሚሳተፉ ይጠበቃል ብለዋል።

እንዲሁም ከአባላት ሀገራቱ ውጭ ያሉ የሀገራት መሪዎችና 13 የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ይሳተፋሉ ብለዋል።

የዘንድሮው የመወያያ አጀንዳ አፍሪካና ትምህርት መሆኑን ገልጸው፤ በመድረኩ ኢትዮጵያ በዘርፉ ያላትን ልምድ የምታካፍል መሆኑን ገልጸዋል።

ከዋናው ስብሰባ ጎን ለጎን በኢትዮጵያ አዘጋጅነት ሁለት ትልልቅ ጉባኤዎች እንደሚካሄዱ ጠቁመው፤ ዝግጅቱ በአድዋ መታሰቢያ የሚካሄድ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው ሁለቱ ጉባኤዎች “የዲጂታላይዜሽን መስፋፋት ለአፍሪካ ትራንስፎርሜሽን” የሚል እና “የአፍሪካ የምግብ ሉአላዊነትን ማረጋገጥ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *