በክልሉ በሺሽንዳ እና በደካ ከተማ አስተዳደሮች ህዝባዊ ውይይት መካሄድ ተጀምሯል::

Spread the love

በሺሽንዳ እና በደካ ከተማ አስተዳደርሮች ከተለያዩ ማህበራዊ መሠረቶች ከተወጣጡ ማህበረሰብ ጋር ከተማ አቀፍ ውይይት እየተካሄደ ነው።

ህዝባዊ ውይይቱ ምልዓተ ህዝቡ ስለአጠቃላይ ሀገራዊ ፖለቲካ ፣ኢኮኖሚያዊ ፣ማህበራዊ ና የሠላም ሁኔታ ላይ በበቂ ሁኔታ ከመንግስት ጋር በመወያየት ለመፍትሔው የጋራ ርብርብ ለማድረግ አስፈላጊ መሆኑም ተገልጿል።

በውይይቱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ፣ የክልሉ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፀሀይ ደርጫ የክልሉ ስነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮምሺን ኮምሽነር አቶ ሙሉሰዉ ዘዉዴ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የወጣቶች ሊግ ኃላፊ አቶ ባርዱላ ኦለኬቦ፣ የካፋ ዞን እና የሺሽንዳ እና የደካ ከተሞች አመራሮች እንዲሁም ከተለያዩ ማህበራዊ መሠረት የተወጣጡ የከተማ ነዋሪዎች በመድረኩ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *