በጤና ተቋማት በወሳኝ ኩነት ምዝገባ የተገኘውን ተሞክሮ በመውሰድ በባለቤትነት ወደ ሌሎች በማስፋት ለተሻለ አፈጻጸም መረባረብ ይገባል፦ አቶ በላይ ተሰማ

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በቅንጅት በተሰሩ የ2017 በጀት ዓመት የተግባር አፈጻጸም ግምገማ መድረክ በቦንጋ አካሂደዋል።

በውይይቱ ላይ በ2017 ዓ/ም በተፈጸሙ ተግባራት ዙሪያ የተደረገ የድጋፊና ክትትል ግብረ መልስ የተሞክሮ ቅመራ፣ ምዝገባ የጀመሩ የጤና ተቋማት የልደትና ሞት የ2017 ዓ/ም የኩነት አፈጻጸም ሪፖርት እና የአመያ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ምርጥ ተሞክሮ ለተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በተሰራው ቅንጅታዊ ስራ በ2017 ዓ/ም በ56 ተቋማት የተከሰቱ የሞትና የልደት የምዝገባ ተግባር አፈጻጸም በልደት 37,836 ከተከሰተው 8502 መመዝገቡ እና በሞት 270 ከተከሰተው 43% መመዝገቡ ተጠቁመዋል።

እንደ ክልል በ2017 ዓ/ም በ5 ኩነቶች 73,087 ለመመዝገብ ታቅዶ 72,350 አፈጻጸሙ 98% መሆኑን በማንሳት በሞት ኩኔት ምዝገባ ሂደት በቀጣይ ትኩረት እንደሚሻ ተገልጿል።

የውይይቱ በግምገማው የተለዩ የአፈጻጸም ክፍቶችን በጋራ በማረም ቅንጅትና ቁርጠኝነት በመጨመር ለላቀ ውጤት በጋራ መስራት እንደሚገባ አንስተው ከሰለጠነ የሰው ኃይል በቀበሌ መዋቅር ያለው ውስንነትና በጤና ተቋማት የመዋቅር ችግር እንዲፈታ ተሳታፊዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ።

መድረኩን የመሩት የክልሉ የመንግሰት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ ወሳኝ ከነቶች ምዝገባ ዜጎች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን በፍትሐዊና ቀልጣፋ መንገድ እንዲያገኙ ለማስቻል ጉልህ ሚና ስለሚኖረው በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከሰው ኃይልና ከመዋቅር ጋር ያለው ችግር ደረጃ በደረጃ በቅንጅት እንደሚፈታ ተናግረው በየደረጃወው ያሉ ባለሙያዎችንም በክትትል ወደስራ ሊገቡና ውጤት ማስመዝገብ ይገባል ብለዋል።

በመሆኑም በአንዳንድ አካባቢ በጤና ተቋማት የተመዘገቡ ተሞክሮዎችን በመውሰድ ያጋጠሙ ማነቆዎችን በመፍታት የታዩ ችግሮችን በቀጣይ በባለቤትነት ማረም እንደሚገባ ተናግረዋል።

የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙ የልደትና ሞት መረጃዎችን በቁርጠኝነት በመስራት የዜጎች አገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል እርካታውን ለመጨመር አስተዋጽኦ ለማበርከት መረባረብ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በየጀረጃው ያሉ የባለድርሻ አካላት ተቋማትን በመደገፍ የህዝብና የቤት ቆጠራ በመዘገየቱ የሚከሰቱ የመረጃ ክፍቶችን ለመሸፈን የሲቭልና ቤተሰብ ምዝገባ ላይ ኃላፊነትን መወጣት አለበት ብለዋል።

የክልሉ ሠላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊና የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሠለሞን ደነቀ የመድረኩ ዓላማ በቀጣይ ትስስር ለመፍጠር፣ ጠንካራና ደካማ አፈጻጸሞችን በመለየት ያጋጠሙ ችግሮችን በቅንጅት ለመፍታት የባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት እንዲነሱ ለማስቻል እንደሆነ ገልጸዋል።

የዘርፍ ተግር አፈጻጸም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መምጣቱን በማስታወስ ከጤና ተቋማት ጋር ያለውን ቁርኝት በማጠናከር ሁሉም አካባቢ ባሉን ተቋማት ወጥ ወደ ሆነ አፈጻጸም ለመድረስ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንደሚሻ አንስተዋል ።

በመጨረሻም በ2017 በጀት ዓመት ከጤና ቢሮ ጋር በቅንጅት በተሰራው ስራ የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የአመያ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ ዋቻ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል እና ገ/ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣታቸው እንዲሁም በስሩ ለሚገኙ የአዋላጅ ክፍል አስተባባሪዎች የዕውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር ተካሂደዋል።

በጌታሁን ግርማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *