



የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ረቂቅ ስታንዳርድ ውይይት እና “ከማዘውተሪያነት ወደ ስብዕና ማበልጸጊያነት” የንቅናቄ መድረክ በሚዛን አማን ከተማ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ረቂቅ ስታንዳርድ ውይይት እና “ከማዘውተሪያነት ወደ ስብዕና ማበልጸጊያነት” የንቅናቄ ሰነድ ቀርቦ ውይይት የተደረገ ሲሆን ሀገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቱ ትውልድ ጊዜውን በአግባቡ መጠቀም እንዲችል የወጣት ስዕብና መገንቢያ ማዕከላት የጎላ ሚና እንዳለው ተመልክቷል፡፡
በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ወጣቱን ወደ ወጣቶች ስብዕና ማዕከላት ማምጣት እና ማዕከሉ ለወጣቶች ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጥ ቅንጅታዊ አሠራር፣ የድጋፍና ክትትል ሥርዓት ማጠናከር እንደሚጠበቅ የመድረኩ ተሳታፊዎች አንስተዋል።
ለዚህም የተቀመጡ ስታንደርዶችን በማደራጀት ስራ ላይ እንዲውል ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ገነት መኩሪያ እንደገለጹት፤ የወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት ለወጣቱ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ስታንዳርድ በማዘጋጀትና በመመሪያ በማስደገፍ ስራ ላይ እንዲውል ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
ለዚህም ህዝቡን በማስተባበርና ቁጣባን በማጠናከር ስብዕና ልማት ማዕከላትን በማስፋት ወጣቱን ወደ ስብዕና ማዕከላት ማምጣቱ ተጠቀሚነታቸውን እያረጋገጡ መሄድ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት፡፡
ወ/ሮ ገነት አክለውም ወጣቱ ወደ ወጣቶች ስብዕና ልማት ማዕከላት መጥቶ በሚጠቀምበት ወቅት መብትና ግዴታውን እንዲያውቅ የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን በመስጠት ግንዛቤያቸውን ማሳደግ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
እያደገ የመጠው የወጣቶች ቁጥርና ፍላጐት አንጻር ማዕከላት ያላቸው ተደራሽነት አነስተኛ ከመሆኑም በላይ አገልግሎት አሰጣጠቸው የወቅቱን የወጣቶች ፍላጐት ያማከለ አለመሆንና ሁለንተናዊ ስዕብናቸውን ከማበልጸግ አንጻር ሰፊ ውስንነቶች መኖሩንና ማዕከላት በስታንዳርድ መሠረት መስራት ተገቢ መሆኑንና ለተግባራዊነቱ ሁሉም የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ አሳስበዋል።
የቢሮው ምክትልና የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ አያሌው ከይሳ በክልላችን 40 ከመቶ የሚሆን ቁጥር የያዙ ወጣት መሆኑንና ይህን ሰፊ ቁጥር የያዘውን የወጣት ኃይል ስዕብናው የበለፀገ ለሀገሩ የሚያስብ አእምሮ የበለፀገ ወጣት መፍጠር ወሳኝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
90 የወጣቶች ስብዕና ማዕከላት በከተማ፣ በወረዳ እና በቀበሌ ድረስ መደራጀቱን ለነዚህ ማዕከላት ስታንዳርድ በማዘጋጀት በቀጣይ ማዕከላትን ከማዞተሪያነት ባሻገር ስብዕና ማበልጸጊያነት እንዲሆኑ ማደራጀቱ ለኢኮኖሚ፣ ለማህበራዊና ለፖለቲካ ዘርፍ የሚያስገኘው ጠቃሜታ የጎላ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማህበራዊ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቤርጉ ጾማ በበኩላቸው፤ ወጣቱን ክፍል አካላዊ፣ አእምሮአዊና ስነ ልቦናዊ ጤንነቱን በመጠበቅ ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ ለሀገራችን ብልጽግና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለዘህም መንግሥት ተሳትፎና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ የሚደረጉ አደረጃጀቶችንና አሰራር ማዕቀፎዎችን በመቅረጽ የወጣቶች ቁጥርና ፍላጐት መሠረት ያደረገ አገልግሎት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በተከተል ወ/ሚካኤል
