ፈጣንና ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት ለመዘርጋት በየደረጃው የሚገኙ የኮሙኒኬሽን ተቋማት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸዉ መስፍን ወዳጆ (ዶ/ር) ገለጹ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች በዳውሮ ዞን መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ማጠቃላያ ድጋፋዊ ክትትል አድርጓል።

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በዞኑ የሚገኙ ኮሙኒኬሽን ተቋማትን ድጋፋዊ ክትትል ሲያደረጉ ቆይተው ዛሬ በዞን ማዕከል የዞኑን የ2018 የግማሽ አመት አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ አጠቃሏል።

ዶ/ር መሰፍን በዚሁ ወቅት እንደገለፁት በሕዝቡና መንግሥት መካከል ፈጣንና ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓት እንዲኖር ለማስቻል በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ተቋማት ተቀናጅተው መስራት እንዳለባቸዉ አሳስበዋል።

ተአማኒነት ያለው እና ትክክለኛ መረጃ ለማህበረሰቡ ለማዳረስ የመረጃ ምንጮችን በመለየት በትኩረት በመገምገም ተቀራርቦ እና ተናቦ በመስራት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የዳውሮ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ፓለቲካና ህዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ቶማስ በበኩላቸው የሚዲያ ተቋማት በመንግስትና በፓርቲ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን ለማስተዋወቅ እና ለማጉላት ጎልህ ሚና እንዳለው አመላክተዋል።

እንደ ሀገር የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማሰቀጠል እየተደረገ ባለው ጥረት የሚዲያ ተቋማት የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ ያሉት አቶ ኢዮብ የኮሙኒኬሽን ተቋማትን መደገፍ እና መከታተል ይጠበቅብናል ብለዋል።

የዳውሮ ዞን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ ሲሳይ በማጠቃለያ መድረኩ የበጀት ዓመቱን የሁለተኛ ሩብ ዓመት ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

በኮሙኒኬሽን ተቋማት የሚከናወኑ ተግባራትን ከማሳለጥ ረገድ ማነቆ የሚሆኑ መሠረታዊ የሆኑ የግባአት፣ የሰው ሀይል ችግሮችን ለመፍታት የሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል።

በመድረኩ ለተነሱ ሀሳብ አስተያየቶች በክልሉ ልዑካኑ ምላሽ፣ ማብራሪያና ግብር መልስ በመሰጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

በማጠቃለያው መድረኩ የሁሉም ወረዳ እና ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የዞኑ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ባለሙያዎች መሳተፋቸዉን የዞኑ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *