




በክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በካፋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎችና ቦንጋ ከተማ አስተዳደር መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሲደረግ የነበረው የድጋፋና ክትትል ግብረ-መልስ ሪፖርት ቀርቧል።
መድረኩን የመሩት የድጋፍ ቡድኑ መሪ ወ/ሮ በረከት ኢዮብ እንዳሉት በተቋሙ የተጀመረው ዓላማ ተኮር ተግባቦት ሥራ የኮሙኒኬሽን ዘርፉን ስኬታማ እያደረገ ነው ብለዋል::
የካፋ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አዳሙ እሸቱ የተቋሙን የ2018ዓ/ም የ6 ወራት አፈፃፀም ያቀረቡ ሲሆን በተመሳሳይ የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የልማት ዕቅድ ዳይሬክተሩ አቶ መልካሙ ሀ/ማሪያም የድጋፍ ቡድኑን ግብረመልስ ሪፖርት አቅርቧል: ።
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ፣ የመንግስት መረጃና ዲጂታል ሚዲያ፣ እንዲሁም የሚዲያ ሞኒተሪንግና ህዝብ አስተያየት ዘርፎች ዋና ዋና ግቦች ግቦች አፈፃፀም በጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ አዳሙ አቅርበዋል።
የመረጃ ሥርዓት ለማዘመን ሳቢና ዓላማ ተኮር ይዘት ከመቅረጽ ጀምሮ ጸጋዎችን ከወትሮ በላቀ ደረጃ በማስተዋወቅ ረገድ በኤሌክትሮኒክስና በህትመት ሚዲያዎች ውጤታማ ሥራዎች ተሰርተዋል ብለዋል።
የሰው ኃይልና የከተማ አስተዳደሮች የመዋቅር ፣ የቁሳቁስና የተሸከርካሪ እጥረት፣ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ውስንነት፣ የፈጠራና ፍጥነት ክፍተት እንዲሁም የሚዲያ አማራጭችን አሟጦ የመጠቀም ክፍተቶች መኖራቸው ተጠቅሷል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በጀትና ዕቅድ ዝግጅት ክትትል ዳይረክቶሬት ዳይረክተሩ አቶ መልካሙ ሀ/ማሪያም የተመረጡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የዞን ማዕከል የድጋፍ፣ ክትትልና ምልከታ ሪፖርት አቅርበዋል።
አቶ መልካሙ ሀ/ማሪያም በሪፖርታቸው እንዳሉት ምልከታ በተካሄደባቸው ሁሉም መዋቅሮች በርካታ ጠንካራ አፈፃፀሞችን መመልከት መቻላቸውን ተናግረዋል::
የተናበበና ዓላማ ተኮር ተግባቦት፣ የሚዲያ ግንኙነትና ይዘት ሳቢነት፣ የህዝብ አስተያየትና ሚዲያ ሞኒተሪንግ ሥራዎችን በጥናትና ምርምር ማስደገፍ የትኩረት አቅጣጫ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሀሰተኛና የተዛባ መረጃ ሥርዓት ታግሎ ሥርዓት ከማስያዝና ትክክለኛ መረጃ ለማህበረሰቡ እንዲደርስ ከማድረግ አኳያ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ ተመላክቷል።
በድጋፍና ክትትል ወቅት በሁሉም ዘርፍ የታዩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እና የተስተዋሉ ውስንነቶችን በማረም ወቅቱን የዋጀ ዓላማ ተኮር የተግባቦት ሥርዓት መዘርጋትና የመረጃ ሥርዓቱን ማዘመን እንደሚጠበቅ አቶ መልካሙ ሀ/ማሪያም ገልጸዋል።
በቀረቡት ሪፖርቶች መነሻ የወረዳና የከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊዎች ሀሳብ አስተያየት በማንሳት ውይይት ተደርጓል።
መድረኩ የኮሙኒኬሽን ተቀማት ያሉበትን ደረጃ በተጨባጭ ያሳዬና አዳዲስ ዕውቀቶች ያስጨበጠ ከመሆኑም በላይ ለቀጣይ ተልዕኮዎች ተጨማሪ አቅም እንደፈጠረላቸው ተሳታፍዎች ተናግረዋል።
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ አስተባባሪ ወ/ሮ በረከት ኢዮብ እንዳሉት ተቋሙን ስኬታማ ለማድረግ የሚደረግ ጥረት የሚበረታታ ነው ብለው የኮሙኒኬሽን ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
በሁሉም ዘርፎች የዘመነ የኮሙኒኬሽን ሥርዓት በመዘርጋት በመፍጠን በመፍጠር በህዝብና መንግስት መካከል ጠንካራ ድልድይ ሆኖ ማገልገል ይገባልም ማለታቸዉን የዘገበዉ የካፋ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው ።
