“ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በትኩረት ይሰራል።አቶ ፍቃዱ ተሰማ

Spread the love

“ጠንካራ አደረጃጀት ለጠንካራ ፓርቲ” በሚል መሪ ሀሳብ በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ሲካሄድ የነበረዉ የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ የ2018 የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቋል።

የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ፍቃዱ ተሰማ እንደተናገሩት ያለፉት ስድስት ወራቶች ይህን ግዙፍ ፓርቲ የሚመጥን ጠንካራ አደረጃጀት ለመገንባት አደረጃጀቶችን ማየት፤ መፈተሽ፣ መልሶ ማደራጀትና ለማብቃት የተከናወኑ ተግባራት የሚበረታታና ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

የሚገጥሙንን ፈተናዎች በመደመር መንግስት እሳቤና እይታ ወደ ዕድል በመቀየር የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ በትኩርት ይሰራል ብለዋል።

በየደረጃው የሚታዩ ቁልፍ ችግሮችን በአግባቡ በመለየት አደረጃጀትን እንደ ግብ በማየትና በውጤት በመለካት በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባም አቶ ፍቃዱ አሳስበዋል።

ባለፉት ስድስት ወራቶች ዉስጥ የተመዘገቡ ዉጤቶችን በማላቅ፤ ዉስንነቶችን የቀጣይ 6 ወራት እቅድ አካል በማድረግ ወደ ጥንካሬ በመቀየር ጠንካራ አደረጃጀት መፍጠር እንደሚገባ አክለዉ ገልፀዋል።

የብልፅግና ፓርቲ ምክር ቤት አባል እና የብልፅግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ም/ኃላፊ የሆኑት አቶ ካሊድ አልዋን በበኩላቸው የፓርቲውን አሰራርና መመሪያዎችን በአግባቡ በመረዳት ለተግራዊነቱ በትኩረት መስራት ጠንካራ ፓርቲ የመገንባት ሂደት ዉስጥ መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም የአደረጃጀት መዋቅር ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።

በመድረኩ በፓርቲው የተዘጋጁ የተለያዩ የአሰራር መመሪያዎች አተገባበር ዙሪያ ሰነድ ቀርቦ ውይይት በማድረግ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል።

ከሁሉም ክልሎች እና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የተወጣጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች ከግምገማ መድረኩ ጎን ለጎን በሰመራ ከተማ የምዕራፍ አንድ አካል የሆነውን ኮሪደር ሙዚየም በሚል የተሰራውን የኮሪደር ልማት ስራዎች እና በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የግብርና እና የሌማት ትሩፋቶችን ስራዎችን ጎብኝተዋል።

ከተሞችን ለነዋሪዎች ምቹ እና ፅዱ ለማድረግ በሰመራ ከተማ እየተሰራ ያለዉ የኮሪደር ልማት የከተማዋን ገፅታ ሙሉ በሙ መቀየሩን እና በግብርና ዘርፍ በክልሉ የተሰሩ የልማት ስራዎች የኢትዮጵያን ብልፅግና አይቀሬነት የሚያሳዩ ተግባራት መሆናቸዉ ጎብኚዎቹ ገልፀዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *