“ባለፉት ስድስት ወራት ባከናወናቸው የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ስራዎች ወደ ላቀ ምዕራፍ የተሸጋገሩ ውጤቶች ተመዝገበዋል።” ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር)

Spread the love

የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ በ2018 ዓ.ም የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በባህርዳር ከተማ ሲያካሂድ የነበረው መድረክ ተጠናቀቀ።

በግምገማ መድረኩ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2018 ዓ.ም የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱም የተገኙት የብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ሚኒስትር ሰማ ጥሩነህ (ዶ.ር) “ባለፉት ስድስት ወራት ባከናወናቸው የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ስራዎች ወደ ላቀ ምዕራፍ የተሸጋገሩ ውጤቶች ተመዝገበዋል” ብለዋል።

በፓለቲካ ስራዎቻችን የሚፈፀሙ ተግባራትን ወጥ በሆነ መንገድ በቅንጅት እና በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ማከናወን መቻሉ ለሀገራዊ ሰላም፣ እድገት እና ብልፅግና የላቀ አስተዎፅኦ አበርክቷል በማለት ተናግረዋል።

በሚካሄዱ ውይይቶች ህዝቡን በአስተሳሰብና በተግባር ከፓርቲና ከመንግስት ጎን እንዲሰለፍ በማድረግ የሰላም ግንባታ ስራዎቻችንን በአስተማማኝ ደረጃ ማድረስ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢትዮጵያ ከልመና እና ከተረጅነት እንድትላቀቅ በሁሉም ክልሎች ሰፊ ሥራ መሠራቱን ገልፀዋል እንዲሁም የብዝኃ ዘርፍ የኢኮኖሚ እሳቤን የሚከተለው ብልጽግና ፓርቲ በሁሉም ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝም አመላክተዋል።

ለዚህም ብልፅግና ፓርቲ ትናንትን፣ ከዛሬና ነገ ጋር አሰናስሎና አስተሳስሮ ለትውልድ ምንዳ ማውረስ የሚያስችሉ ስኬታማ ስራዎችን አከናውኗል ነው ያሉት።

የኑሮ ውድነት ቅነሳ እና የስራ እድል ፈጠራ ስራዎችን በቀጣይ ወራት ልዩ ትኩረት ሰጥተን መስራት ይገባናል ብለዋል።

በግንቦት ወር የሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ነፃ፣ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲከናወን ብልጽግና ፓርቲ የድርሻውን ለመወጣት ከወዲሁ ዝግጅት እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።

#Prosperity

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *