
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ 23 ነጥብ 46 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክ በ2016 በጀት አመት አጋማሽ በሺፒንግ ዘርፍ ፣ በጭነት አስተላላፊነት ፣ በወደብና ተርሚናል አገልግሎት እንዲሁም በኮርፖሬት አገልግሎት ዘርፍ የተለያዩ ስራዎችን ማከናወኑን ገልጿል።
በዚህም በመጀመሪያው ግማሽ ዓመት ከሚሰጡ አገልግሎቶችና ከሌሎች የገቢ ምንጮች 17 ነጥብ 23 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 23 ነጥብ 46 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ተመላክቷል።
ከዚህም ውስጥ ሶስት ነጥብ 26 ቢሊዮን ብር ከታክስ በፊት የተገኘ ትርፍ ሲሆን በግማሽ ዓመቱ የድርጅቱን መርከቦችና የኪራይ መርከቦችን በመጠቀም 1 ሚሊዮን 886 ሺ 399 ቶን ዕቃ ለማጓጓዝ ታቅዶ 2 ሚሊዮን 214 ሺ 156 ቶን ማጓጓዝ እንደተቻለ ተጠቅሷል።
የገቢና ወጪ ኮንቴይነር ፍሰት 197 ሺ 699 TEU ኮንቴይነር ለማድረስ ታቅዶ 204 ሺ 358 TEU ኮንቴነር መስተናገዱንም የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ መረጃ ያመለክታል።
በማኑፋክቸሪንግና በወጪ ንግድ ስራ ላይ ለተሰማሩና ለተፈቀደላቸው ባለሃብቶች ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ከሚሰጣቸው ድጋፎች ውስጥ በወጪ ንግድ ላይ ለተሰማሩ ባለሃብቶች ለምርት ግብአትነት ለሚያስገቧቸው ጥሬ ዕቃዎች፣ ከየብስ ትራንስፖርት የትርፍ ህዳግና ከባህር ትራንስፖርት የትርፍ ህዳግ የዋጋ ቅናሽ ማድረግ ይገኙበታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
