ለዘላቂ ሰላም መረጋጋጥ እና የሕግ በላይነት መከበር በየደረጃው ቅንጅታዊ አሠራሮችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተመላከተ

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የዞኖች የፀጥታ ምክር ቤት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።

በክልሉ በካፋ ፣ ቤንች ሸ እና በካፋ ዞኖች የጸጥታ ግብረ ኃይል የምክክር መድረክ የተካሄደ ሲሆን፤ መድረኩም በዞኖች አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ እና የህግ በላይነት ማስከበር ላይ ትኩረት ያደረገ ነዉ።

በመድረኩ ህገወጥና የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ መከላከል እና መቆጣጠር፣ የውስጥ አንድነት ማጠናከር፣ በድንበር አከባቢ የሚስተዋሉ የፀጥታ ስጋቶችን መለየትና በውይይት መፍታት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል።

በዚህም በየደረጃዉ ቅንጅታዊ አሠራሮችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ የተጠቀሰ ሲሆን በሂደቱም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ይጠበቅባቸዋልም ተብሏል።

በየአካባቢው የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ እንዲሁም የጋራ እሴቶችን እና የአከባቢን ገጽታ ለማበላሸት በማህበራዊ ሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃዎችን የሚያሰራጩ አካላትን መመከትና የህግ በላይነትን ማስከበር እንደሚገባም ተጠይቋል።

በዞኖች በተካሄዱ የጸጥታ ግብረሃይል ምክክር መድረኩ በአካባቢው አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም በማስፈን የተጀመሩ የልማትና ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ለማሳደግ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል።

በመድረኩ የክልሉ ሠላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊዎች፣ የዞን ዋና አስተዳዳሪዎች እና ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ የሚመለከታቸው የሠላምና ጸጥታ አካላት መመገኘታቸዉን የዞኖች ኮሙኒኬሽን መረጃዊች ያመለክታል

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *