የመኖሪያ ቤት ችግርን በዘላቂነት ለመቅረፍ የሞርጌጅ ሥርዓትን ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነዉ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን በተለይ ከመኖሪያ ቤት አቅርቦት ጋር ተያይዘዉ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመቅረፍ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የቤት ልማት ፖሊሲ በቅርቡ መጽደቁን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በመንግስት፥ በግል፥ በመንግስትና በግል አጋርነት 1.5 ሚሊየን ቤት ለመገንባት ሰፋፊ ስራዎች መጀመራቸዉን ተናግረዋል፡፡

የቤት አልሚዎችና ገዢዎች ከባንኮች ጋር በመዋዋል ቤት የሚያለሙበት የሞርጌጅ የአሠራር ስርዓት ኢትዮጵያ ዉስጥ እስካሁን ድረስ አለመኖሩን በማንሳት ቤት አልሚዎችም ሆኑ ቤት ገዢዎች ሳይጎዱ ከባንኮች ጋር ተዋዉለው ቤት የሚያገኙበትን አሠራር ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

አሠራሩን በኢትዮጵያ ዉስጥ ለመተግበር የባንክ፥ የመሬት፥ የዲዛይን፥ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን ፖሊሲም እየተዘጋጀ ነዉ ብለዋል፡፡

የሞርጌጅ የአሰራር ስርዓትን ለመጀመር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲጠናቀቁ ይፋ እንደሚደረግም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *