የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች ቦንጋ ከተማ ገቡ

Spread the love

የተለያዩ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ቦንጋ ከተማ ገብተዋል።

ወደ ክልሉ ከገቡት የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች መካከል የዓለም ጤና ድርጅት (WHO)፣ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO)፣ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO)፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ቢሮ (OCHA) እና ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ይገኙበታል።

የተባበሩት መንግስታት የሥራ ኃላፊዎችና ተወካዮች ወደ ቦንጋ ከተማ ሲደርሱ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)ን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ መንግስት ሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የልማት አጋሮቹ በክልሉ በሚኖራቸው ቆይታ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ከመጎብኘት ባሻገር በንፁህ መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን በጤና እና ትምህርት ዘርፍ እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ የሚቋቋም ግብርና ሥርዓት በመዘርጋት ዙሪያ ከክልሉ መንግሥትጋርውይይት የሚያደርጉና የቀጣይ ድጋፍ አቅጣጫ የሚለዩ ይሆናል::

ፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *