የብሔረሰቡ ቋንቋና ታሪክ ላይ በደንብ ለመስራት የተቀናጀና ቀጣይነት ያለውን ሥራ እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ

Spread the love

የማጃንግ ብሔረሰብ የቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም የብሔረሰቡ ተወላጆችና ወዳጆች በተገኙበት በሸካ ዞን ቴፒ ከተማ ፓናል ውይይት አካኺዷል ።

የፓናል ውይይቱን መነሻ ነጥቦች የሚጠቁም ሰነድ ያቀረቡት የደቡብ ምዕራብ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ጸ/ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ እንዳሻው: ብሔረሰቡ ከጥንት ጀምሮ የራሱ የሆነ ባህላዊ ክዋኔ፣ ቋንቋ፣ ወቅትና ወራት አቆጣጠር ያለው ህዝብ መሆኑን አሳይተዋል።

በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ አያያዝ እስከ ዓለም በዩኔስኮ በተመዘገበው ባዮ-ሪዘርቭ የታወቀው ማጃንግ ብሔረሰብ: በዛፎች ዑደት ወይንም አበባ መሠረት ወቅትና ወራትን እንደሚቆጥር በጥናታዊ ጽሑፉ አብራርተዋል።

ለብሔረሰቡ ታሪክና ቄንቋ ዕድገት ዘርፈ ብዙ ስራዎች ተሠርተው ውጤት መምጣቱን ያመላከቱት አቅራቢው: የናይሎ ሳሀራ ቤተሰብ የሆነውን ማጃንግ ቋንቋን ተማሪዎች እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ ከመማራቸው ባሻገር እስከ ኮሌጅ ደረጃ እየተሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ብሔረሰቡ በእርሻ ዘርፉ የሚያሳየው ታታሪነትና እንግዳ ተቀባይነትን በማጠናከርና የውስጥ አንድነትን በማምጣት ያንኑ አንድነት ለልማትና ሠላም ግንባታ ማዋል እንደሚያስፈልግ አቶ ተስፋዬ አሳስበዋል።

የዛሬው ታሪካዊ ቀን የማጃንግ ብሔረሰብ ደግም የተወለደበት ቀን ነው ብለው የተቀበልነውን የፍቅር ዕዳና ኃላፊነት እስከ ዳር ማድረስ ይጠበቅብናል በማለት አጽነረኦት የጋምቤላ ክልል አፈ-ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ መሠረት ማቴዎስ ናቸዉ።

ሁነቱ ቀጣይነት የሚኖረውና ለብሔረሰቡ ባህልና ቋንቋ ዕድገት የሚሰራ መሆኑን ያመላከቱት ክብርት አፈ-ጉባኤዋ: በዚሁ ወንድም ለወንድም ግንኙነት ለጋራ ሠላምና ልማት ተቀናጅተው ለመስራት መሠረት የጣለ እንደሆነ ገልጸዋል።

ወጣቱ ትውልድና ተመራማሪዎች በዛሬው ጥናታዊ ጽሑፍ መሠረት መልሰው በማጥናትና በመመራመር ለቀጣዩ ትውልድና ቀሪ ዓለማት የማስተዋወቁን ስራ እንዲያጠናክር አሳስበዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት:- አሁን ሀገሪቱን እየመራ ያለው የለውጡ መንግስት ከዚህ ቀደም የነበረውንና ያለተፈቀደልን ዕድል ሰጥተውን በዚህ ደረጃ እንዲንነሳ ማድረጉ በብሔረሰቦች እኩልነት የሚያምን ስርዓት መሆኑን የሚያሳይ እንደሆነ ገልጸዋል።

ለፓናል ውይይቱ መነሻነት የቀረበው ሰነድ የብሔረሰቡን ታሪካዊ አመጣጥና አኗኗሩን የዳሰሰ ነው ብለው: በሀለቱም ክልሎች ውስጥ ያለት የብሔረሰቡ ተወላጆች ተቀራርበንና ተቀናጅተን ለአካቢው ሠላምና ልማት እንዲሁም ለቋንቋው ዕድገት ሊንሰራ ይገባል ብለዋል።

የዚህ ታሪካዊ ሁነት አስተባባሪዎች ለሀገራችን አንድነትና ብልጽግና መሠረት እንደጣላችሁ ይሰማናል ያሉት አስተያየት ሰጪዎቹ በተለይ የሸካ ዞን ቴፒ ከተማ የህብረ-ብሔራዊነት መገለጫ መሆኗ በድጋሜ ከፍ ብሎ የታየበት ዕለት መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *