






ርዕሰ መስተዳድር ኢንጃነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በተገኙበት በታርጫ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።
ምክር ቤቱ በጉባኤው በመጀመሪያ ቀን ውሎ የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚ ተቋማት የ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ረፖርት ቀርበው በምክር ቤት አባላት ተገምግመው ማጽደቁ የሚታወቅ ነው።
ምክር ቤቱ በዛሬው ቀን ውሎ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆች እንዲሁም የተለያዩ ሹመቶችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በፍቅር ከበደ
