






የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመስተዳድር ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 48ኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አስተላልፏል ፡፡
በዚህም መሠረት፦
1ኛ.በክልሉ በተጨማሪነት እየተሰሩ ያሉ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ ሥራዎች ያሉበትን ደረጃ ገምግሟል።በዚህ በተጨማሪነት እየተሰሩ ያሉ አምስት የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት በፍጥነት አልቀዉ ለአገልግሎት ዝግጁ እንዲሆኑ አቅጣጫ አስቀምጧል።
2ኛ. መስተዳድሩ ምክር ቤቱ በሁለተኛ አጀንዳነት የሞዴል ገጠር መንገድ ግንባታን አፈጻጸም ገምግሟል። በክልሉ በ10 ወረዳዎች እየተሰሩ ያሉ የሞዴል ገጠር መንደር ግንባታ በፍጥነት እየተሰሩ መሆኑን ገምግሟል ። በዚህም ግምገማዉ የተጀመሩ 10 ሞዴል መንደሮች እያንዳንዳቸዉ 100 ሞደል ቤቶችን በዉስጣቸዉ ሁሉንም ፓኬጅ ባሟላ መልኩ እንዲጠናቀቁ በተገቢዉ ክትትል እንዲደረግ ወስኗል።
3ኛ. ምክርቤቱ በ3ኛ ደረጃ ተጀምረዉ ያልተጠናቁ የተለያዩ ግንባታ ፕሮጀከቶች ማለቅ የሚችሉበት ሁኔታ ላይ ተወያይቶ ተጨማሪ የበጀት ድጋፍ እንዲደረግላቸው ወስኗል ።
