በትብብርና በፉክክር መሐል ሚዛን ማስጠበቅ ያስፈልገናል:- የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት “በትትብብርና በፉክክር መሐል ሚዛን እንጠብቃለን!” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ ጉዳዮችና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ የምክክር መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካኸደ ነው።

የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ግርማ ባሻ ለውይይት የሚሆን የቃል ኪዳን ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት እንደገለፁት የፖለቲካ ፓርቲዎች ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና ለዴሞክራሲ ግንባታ የሚያበረክቱት ሚና አይተኬ ነው ብለዋል።

ተፍካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የህግ የባላይነት እንዲከበር በማድረግ በተፈጠረው ምህዳር: ይዘው የቀረቡት ሀሳብ ላይ ትኩረት ሰጥተው አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመፍጠር መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

ማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ የሚዲያ አጠቃቀም ሀገር በሚጸና መልኩና ጥፋቶችን በማያስከትል መልኩ ሀይል አሰባሳቢ ኮሙኒኬሽን አማራጭ ሀሳብ ብቻ ይዘው መቅረብ እንደሚገባ ገልጸዋል።

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሐዊ፣ ሠላማዊና ተዓማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በኃላፊነትና ለሀገራችን ዘላቂ ዕድገት ካለው ፋይዳ አንጻር መንቀሳቀስ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የዲህረ ምርጫ ጊዜ ላይ ሲደርስ አባሎቻችንና ደጋፊዎችን ህዝቦችን በማመስገን ወደ መደበኛና ሀገር ልማት ስራ ለመግባት እንደሚያስፈልግ የተገለጸ ሲሆን ሰነዱ ላይ ውይይት ተደርገው እንደሚፈራረሙ ማወቅ ተችለዋል።

በአሻግሬ ገ/ወልድ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *