ጥራት ያለው መረጃ ለክልሉ ሁለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ

Spread the love

በሚዛን አማን ከተማ እየተካሄደ በሚገኝ የምክክር መድረክ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2017 በጀት ዓመት የሶሽዮ-ኢኮኖሚ መረጃ የማጥራትና የካፒታል ፕሮጀክቶች ዝግጅት ላይ ትኩረት ተደርጓል።

የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ በመድረኩ እንደገለጹት፤ ክልሉ አጠቃላይ ማክሮ ኢኮኖሚውን ውጤታማ ለማድረግ ወቅቱን የዋጀ የዕቅድና ሪፖርት ሥርዓት ዘርግቷል። በተለይምዕቅዶችና አፈጻጸሞች በቴክኖሎጂ የታገዙ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው።የካፒታል ፕሮጀክቶች ለሕዝቡ ተጨባጭ ጥቅም እንዲሰጡ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

የመረጃ ልውውጥን በተመለከተ አንዳንድ ተቋማት መረጃዎችን ለቢሮው የመላክ ክፍተት እንዳለባቸው የጠቆሙት ኃላፊዋ፤ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሬ መረጃዎችን በማጥራትና በማደራጀት ለክልሉ ዕድገት የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ሳምሶን አድማሱ በበኩላቸው፣ የዘርፉን ውጤታማነት ለማረጋገጥ መሰል የባለድርሻ አካላት መድረኮች ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *