




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት ገቢዎች ቢሮ የታክስ ማጭበርበር ወንጀልን ለመዋጋትና የህግ ማስከበር ስራን ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ በቦንጋ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ላይ የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ምክትልና የህግ ማስከበር ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ትዕግስት በላይ እንደገለጹት፤ የታክስ ማጭበርበር ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።
ይህንን እንቅስቃሴ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግም የባለድርሻ አካላት ሚና መጠከር እንዳለበትም አሳስበዋል።
በተለይም ከፖሊስ ኮሚሽን፣ ከፍትህ አካላትና ከሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት፣ የተቋረጡና የዘገዩ የምርመራ መዝገቦችን በአፋጣኝ እልባት ለመስጠት አቅጣጫ ተቀምጠዉ እየተሰራ መሆኑንም ነው ኃላፊዋ የገለጹት።
ይህም የወንጀል ምርመራ ሂደቱን ለማፋጠንና ተጠያቂነትን ለማስፈን ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለውም ነው ወ/ሮ ትዕግሥት በላይ ያመላከቱት።
በውይይቱ ላይ የቢሮው የታክስ ስጋት ስራ አመራር ኦዲት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጎበዜ ጎባና፣ የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል የባለድርሻ አካላትን ሚና ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።
በፍቅር ከበደ
