ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) የክልሉ ክላስተር ከተሞች የቢሮ ግንባታ አፈጻጸም ገመገሙ።

Spread the love

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፥ በክልሉ ሚዛን አማን እና ቴፒ ከተሞች እየተገነባ ያለውን የቢሮ ግንባታ ፕሮጀክት አፈጻጸም ገምግሟል።

ፕሮጀክቶቹ የደረሰበትን አፈጻጸምን በሚመለከት በአማካሪ ድርጅቶች ዝርዝር ሪፖርት ቀርበው የባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተገምግሟል።

ተቋራጩ ግንባታው በተያዘለት ግዜና የጥራት ደረጃ ለማጠናቀቅ በትኩረት መስራት እንዳለበት ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ በግንባታ ስፍራው በቂ ግንባታ ግብዓትና የሰው ሀይል ማቅረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የግንባታ መዘግየት ተፈጥሮ መንግሥት ለአላስፈላጊ ወጪ እንዳይደረግ የአከባቢው መንግሥት ትብብርና ድጋፍ መጠናከር እንዳለበትም ርዕሰ መስተዳድሩ በአጽንኦት አሳስበዋል።

የሚዛን እና የቴፒ ከተሞች የግንባታ ደረጃ በተፈለገው ልክ እየሄደ አለመኾኑን የገለጹት ዶ/ር ነጋሽ፥ የሥራ ተቋራጩ አስቻይ ሁኔታዎችን በመፈጠር ግንባታውን በአጭር ጊዜ ለማጠናቀቅ ትኩረት መስጠት አለበት ብሏል።

ከአካባቢው የሚገኝ የግንባታ ግብዓት በተገቢው ለመንግሥት የልማት ፕሮጀክት መቅረብ እንዳለበት ያሳሰቡት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ፕሮጀክቶቹ የክልሉ መንግሥት ስትራቴጂክ ፕሮጀክቶች መኾናቸውን ገልጸዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በመጨረሻም በሁለቱ የክልሉ ክላስተር ከተሞች እየተገነቡ ያሉ ህንጻዎች አጠቃላይ አፈጻጸም ዝቅተኛ በመኾኑ በቀጣይ አጭር ጊዜ በልዩ ትኩረት መከናወን አለበት ብለዋል።

የሥራ ተቋራጩ በበኩሉ ለግንባታው መዘግየት የተለያዩ ምክንያቶች መፈጠራቸውን በማንሳት፥ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ መጠናከር እንዳለበት ጠይቀዋል።

ማነቆዎች ተፈተው ግንባታውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ቁርጠኛ መኾናቸውን ነው የሥራ ተቋራጩ የገለጸው።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *