




የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትየምግብ ሥርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም በጀት ድጋፍ የተከናወኑ የግብርና ምርምር ስራዎች ዓመታዊ ክልላዊ የግምገማ መድረክ በቦንጋ ከተማ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ በተከናወኑ የምርምር ስራዎች መካሄዱ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ዓለሙ እንዳስታወቁት፣ በምርምር ሂደት ውስጥ በግብርና ዘረፍ ላይ ያሉ ማነቆዎችን በመፍታት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ የምርምር ተግባራት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መገምገም አስፈላጊና ቀጣይነት የሚኖረው ጉዳይ መሆኑንም ገልጸዋል ፡፡
በክልሉ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ ያለውን አቅም መሠረት ያደረጉ የምርምር ስራዎችን እየገመገሙ መሆኑን አንስተው በቀጣይም የግብርና ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የተለያዩ የምርምር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል።
የምርምር ማዕከላትና ተመራማሪዎች ክልሉን አቅም መሠረት ያደረገ እና ችግር ፈቺ የምርምር ስራዎችን በማውጣት፣ በማላመድና ለአርሶ አደሩ በወቅቱ የማውረድ ትኩረት ሰጥው መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና እየቀረቡ ያሉ የምርምር ስራዎች ገምገም ዶ/ር ዋሲሁን ሀሰን፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የቦንጋና የታርጫ የምርምር ማዕከላት በእንስሳት ዘርፍ እየቀረቡ ያሉ ብዙዎቹ የምርምር ስራዎች የህብረተሰቡን ችግር ልቀርፉ የሚችሉ መሆናቸው መገንዘብ መቻላቸውን አንስተው ሀገሪቱ ግብርናን ለማሻሻል እየተከተለች ላለችው የበኩላቸውን የሚወጡ መሆናቸውን አገኝበታለሁ ነው ያሉት።
ተመራማሪዎች ምርምር ይሰራሉ የምርምር ኢንስቲትዩቱ የምርምር ሀሳቦችን እንደሚያቀርብ የገለጹት ዶ/ር ዋሲሁን ሀሰን የግብርናውን ዘርፍ ተግዳሮቶች ለመፍታት እንዲቻል ተቀባይነት አግኝቶ ለዉጤታማነቱም ትልቅ ካፒታል የሚጠይቁ ምርምሮች በተገቢው በበጀት ሊደገፉ እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የእንሰሳት ምርምር ዘርፍ አስተባበሪና የቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ዘላለም አባተ እንደገለጹት፤ እንደ ክልል በእንስሳት ዘርፍ አምስት የሚሆኑ የምርምር ዘርፎች እንዳሉትና ከነዚህም ውስጥ 38 የእንስሳት ምርምር ተግባራት ቀርበው እየተገመገሙ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
በክልሉ ባሉት ሁለት የምርምር ተቋማት የእንስሳት ዘርፍምርትና ምርታማነት ለማሻሻል የተለየዩ የምርምር ዉጤቶችን ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችሉ ተግባራት በተለይም በአነስተኛ አመንዣክ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ስራ እያከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
በቦንጋ ግብርና ምርምር ማዕከል የእንስሳት ዝሪያ ማሻሻያ ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ አድሱ ገ/ሚካኤል፤ ክልሉ በእንስሳት ዘርፉ ለሀገር የሚበቃ በጣም ትልቅ ሀብት ያለው በመሆኑ ይህንን በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል በአነስተኛ አመንዣክ እንስሳት ላይ ትኩረት በማድረግ የምርምር ስራውን እየሰራ መሆኑን አንስቷል።
በተከተል ወ/ሚካኤል
