የ9 ወራት የመንግሥትና ፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ እየተካሄደ ነው

Spread the love

​በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የ2018 በጀት ዓመት ያለፉት 9 ወራት የመንግሥት እና የፓርቲ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

​መድረኩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾን ጨምሮ ሌሎች በየደረጃው የሚገኙ የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ እንደገለጹት፤ በክልሉ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት በየዘርፉ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት በየሩብ ዓመቱ ሲገመገሙ ቆይቷል።

የዛሬው መድረክም ባለፉት ዘጠኝ ወራት በመንግስት እና ፓርቲ የተከናወኑ የሥራ አፈጻጸሞችን በጋራ በጥልቀት በመገምገም፣ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና ድክመቶችን ለማረም ያለመ እንደሆነም ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ አመላክቷል።

በመድረኩ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፣ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸዉን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት እና የፓርቲ ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዚሁ የግምገማ መድረክም የፓርቲው ያለፉት ዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የስትራቴጂክ ሥራ አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አንተነህ አየለ በኩል እየቀረበ ይገኛል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *