


በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ከፍተኛ አመራሮች ውይይት በቦንጋ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።
በውይይቱ መግቢያ ንግግር ያደረጉት የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን፥ የብልፅግና ፓርቲ አባልና አመራሩ ብሄራዊ ጥቅም ለማስከበር በሚያስችል ስትራቴጂካዊ የመሻገሪያ አቅጣጫዎችን በቁርጠኝነት እንዲተገብሩ ጠይቀዋል።
የብልፅግና ፓርቲ በየጊዜው ሀገራችንን የሚገጥሙ ፈተናዎችን የመሻገሪያ ስትራቴጂዎችን በመቀየስ ወደ ዕድል በመቀየር ኢትዮጵያን የአፍሪካ ተምሳሌት ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ፍቅሬ፣
አመራሩ በወቅታዊና ነባራዊ ቀጠናዊ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች ላይ ተቀራራቢ አረዳድ በመያዝ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች በማስከበር የተጀመረው ልማት እንዲቀጥል የበኩላቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ነው አቶ ፍቅሬ ያስገነዘቡት።
ፓርቲው የአመራር የመፈጸም አቅም ለማጎልበት በየጊዜው የሚያዘጋጀው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፤ አመራሩ በፓርቲው የሚወርዱ የኢንሼቲቭና መደበኛ ተግባራት በተደራጀ መልኩ በመፈጸም ውጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝም ነው አቶ ፍቅሬ የገለጹት።
መድረኩ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በአመራሩ መካከል የተቀራረበ አረዳድ በመፈጠር የተጀመረውን የሠላምና የልማት ስራዎችን በማጠናከር ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ ያለመ እንደኾነም ነው አቶ ፍቅሬ የጠቆሙት።
በዕድገቱ በዛብህ
