

ኢትዮጵያ ሀገራችን የብዙ ዓይነት ዕፅዋት መገኛ መሆኗንና ለእነዚህ ዕፅዋት ዓይነቶች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው መዓዛማና መድሃኒታማ የቅመማ ቅመም ዝርያዎች ትኩረት በመስጠት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ሊያበረክቱ በሚችሉ ሁኔታ ጥቅም ላይ ማዋል ይገባል።
የመድሐኒታማና መዓዛማ ቅመማ ቅመም ዕፅዋቶች አመራረትና ጥቅም በተለይም የበሶቢላ፣ ሚንት(ናና)፣ ጦስኝ፣ ሮዝመሪ(ስጋ መጥበሻ)፣ የሴጅ፣ኮሰረት እና ሎሚ አመራረትና አጠቃቀማቸው በማሻሻል የተሻለ ኢኮኖሚ ማግኘት ይቻላል።
ኢትዮጵያ በተለያዩ ስነ-ምህዳር ከምታመርታቸው በርካታ ሰብሎች አንዱ የቅመማ ቅመሞች ምርት ሲሆን የውጪ ምንዛሪ ከሚገኝባቸው ሰብሎችም ተርታ የሚመደብ እና ወደ ሱዳን፣ የመን፣ሳውድ አረቢያ፣ ህንድ፣ተባበሩት አረብ ኢሚሬት፣ ሞሮኮ፣ ሲንጋፖር፣ጆርዳን፣አውሮፓ እና ሌሎች መዳረሻ ሀገራት ግብይቱ እንደሚፈፀም ከመረጃዎች መረዳት ተችሏል፡፡
በተጨማሪም በሀገራችን በርካታ የቅመማ ቅመም ዓይነቶች እንደሚመረቱና በተለይም በመድሃኒት አምራቾች፣በኮስሞቲክስ ምርቶች፣ በመጠጥ፣ በምግብ ኮምፕሌክስ ኩባንያዎች፣ወዘተ የሰብሎቹ ሚና የላቀ መሆኑን ተመራማሪዎቹ ማብራራታቸውንና በመንግስት በኩል የበለጠ ሊሰራበት የሚገባ ዕፅዋት ስለመሆኑ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን መረጃ ያመላክታል ።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ለቡና ምርት እና ለቅመማቅመም ምርት ስነምህዳር ያለው አካባቢ በመሆኑ የተነሳ በዘርፉ በርከት ያሉ አርሶ አደሮችና የንግዱ ዘርፍ ተዋንያን እየተሳተፉበት መሆኑ አይዘነጋም፡፡
ክልሉ ለቡና ምርት ብቻ ሳይሆን በስፋት ከሚመረቱ የቅመማ ቅመም ምርቶች እንደ ኮረሪማ፤ እርድ፤ ዝንጅብል፣ በርበሬ፤ቁንዶ በርበሬ እና ጥምዝ ትልቁን ድርሻ ሲይዙ ከዚህ በተጨማሪ ሌሎች መዓዛማና መድኃኒታማ ቅመማ ቅመም ሰብሎችም በስፋት እየለሙ ይገኛሉ፡፡ ልክ እንደ ቡና ሰብል የቅመማ ቅመም ሰብሎችም በተለያየ ስነ-ምህዳር ተመርተው ለገበያ እየቀረቡ ይገኛል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የቅመማ ቅመም ሰብሎች ሽፋን 86 ሺህ ሄ/ር በላይ የደረሰ መሆኑን የክልሉ ቡና፣ሻይና ቅመም ቅመም ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የቡና፤ሻይና ቅመም ቅመም ልማትና ጥበቃ ዘርፍ ኃላፊ አቶ በላይ ኮጁአብ ገልጸዋል።
ከዘርፉ ለአከባቢ ገበያ የሚቀርበውን ወይም ለቤት ውስጥ ፍጆታ የሚውለውን ሳይጨምር በዓመት እስከ 40 ሺህ 198.73 ቶን ምርት ተመርቶ ለማዕከላዊ ገበያ እንደሚቀርብም አቶ በላይ ተናግረዋል ፡፡
ክልሉ ከቅመማ ቅመም ዘርፍ ብዙ እንዳልተሰራበትና ያለውን ክፍተት በማረምና በመገምገም ትረኩት አድርጎ ወደ ስራ እየገባ ያለው መዓዛማና መድኃኒታማ ቅመማ ቅመም ሰብሎችን የማስፋትና ምርታማነታቸውን ጨምሮ ወደ ገበያ በጥራትና በመጠን እንዲቀርቡ የማድረግ ስራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡
ቅመማ ቅመም ሰብሎቹ ከምግብ ማጣፈጫነት በተጨማሪ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ጋር በያያዝ በትንሽ ማሳ ወይም በጓሮ ደረጃ የተሻለ ገቢ የሚያስገኙ፣ለኢንድስትሪ ግብአት የሚሆኑ ማለትም ለመድሃኒት ፋብርካ ጥሬ ዕቃነት፣ለሳሙናና ሽቶ መስሪያነት በግብአትነት የሚያገለግሉ የጥሬ ዕቃዎች ምንጭ ሲሆኑ፤በሌላ በኩል ደግሞ የአከባቢ አየር የሚጠብቁና አሲዳማ አፈር ተቋቁሞ ምርት መስጠት የሚችሉትም በመካከላቸዉ ያሉ ሲሆን ለባህላዊ መድኃኒትነትም ጭምር የሚውሉ በመሆናቸው ትከረት መስጠት ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል አቶ በላይ ፡፡
ከእነዚህ መዓዛማና መድኃኒታማ ቅመማ ቅመም ሰብሎች በዋናነት በክልላችን የሚለሙ ዝሪያዎች የጥብስ ሳር ወይም ሮዝመሪ፣ ኮሰረት፣ ሎሚናት፣ድንቢላል፣በሶቢላ/ዘቃ ቅቤ/፣ጤናዳም፣ጥቁር አዝሙድ ፣አርቲ፣ላቫንድር..ሲሆኑ ከጠቅላላው የክልላችን የቅመማ ቅመም ሽፋን ወስጥ 158 ሄ/ር ሲሸፍኑ በዚህ ስራ ወንድ 152 ሴት 1450 ድምር 1602 ያህል የሰው ሀይል ከመደበኛ እርሻ ስራው ባሸገር ተሳትፎበታልሲሉ አቶ በለይ ገልጸዋል፡፡
ክልሉ ከመዓዛማና መድኃኒታማ ቅመማ ቅመም ሰብሎች ብቻ ከ2016 በጀት ዓ.ም ግመሽ ዓመት እስከ 418.6 ቶን ምርት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ መቻሉንም አቶ በላይ አብራርተዋል፡፡
በመዓዛማና መድኃኒታማ ቅመማ ቅመም ሰብሎች በክልሉ ካፋ ዞን በግሉ ዘርፍ የሚያበረታታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና ይህንም አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አቶ በላይ ተናግሯል ።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መዓዛማ ዘይቶችና ቅመማ ቅመምን በማልማት በኩል መልካም ጅማሮች ብቅ እያሉ መጥተዋል ።
ዳማሲን የመዓዛማ ዘይቶችና ቅመማ ቅመም ዉጤቶች ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
በካፋ ዞን በ5 ወረዳዎች እና በ38 ቀበሌዎች ቅመማ ቅመሞችን በማቀነባበር ስራ ላይ እንደሚገኝ የማህበሩ ስራአስኪያጅ ተወካይ አቶ ሲሳይ ወ/ስላሴ ተናግረዋል።
ማህበሩ በዋናነት የሚያከናውነው ተግባራት
ቅጠላ ቅጠል ምርቶችን በማድርቅ በማጣራትና በማሸግ ለግብይት በማቅረብ የተሻለ ገቢ ማግኘት ላይ አትኩሮ ነው።
የዕርድ ምርት በመቀሸር በመፍጨት ዱቄት በማዘጋጀትና በማሽግ፣ዝንጅብል ምርት በጥራት
በማድረቅና በመቀሸር ሲሆን እንደየቅመም ባህሪና በደንበኞች ትዕዛዝ መሰረት እንደሚያዘጋጁም ተወካዩ ተናግረዋል ።
አሁን ላይ ስራዉ በተሻለ ደረጃ የሚገኝ ሲሆን ለዚህም ተነሳሽነት ያለዉ የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን አብራርቷል።
በማህበሩ 3 ሺህ 400 ሴቶች በዚህ ስራ ዘርፍ በ10 ማህበራት ተደራጅተዉ አምርተዉ ሽጠዉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ መሆን ችለዋል ሲልም አቶ ሲሳይ ተናግረዋል ፡፡
በዳማሲን ሥራ ላይ በቋምነት ወንድ 4 ሴት 4 ድምር 8 በጊዜያዊ ወንድ 6 ሴት 15 በድምሩ 22
ሠራተኞች ተቀጥረዉ እየሰሩ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።
በቀጣይም ስራዉን በክልል ደረጃ ለማስፋት ከባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት በማድረግ በቤንች ሸኮ ዞን ለማፋት ከስምምነት ላይ በመድረስ ስራውን ለሠጀመር የችግኝ ማባዣ ችግኝ ጣቢያ ማግኘታቸውን እንዲሁ ገልጸዋል፡፡
