በኮንታ ዞን አመያ ከተማ በተለያዩ ኩነቶች የደመቀው የብልፅግና ፓርቲ የድጋፍ ሰልፍ!

Spread the love

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልፅግና ፓርቲ የሚደግፍ ታላቅ ህዝባዊ የድጋፍ ስልፍ እየተካሄደ ይገኛል።

ይህ በነቂስ የወጣው ከፍተኛ ህዝብ ፓርቲው በየደረጃው እያከናወነ ላለው ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞና ለጀመራቸው ዘላቂ የልማት ስራዎች ያለውን ጽኑ አጋርነት በተግባር የሚያሳይ ነው።

የቅስቀሳና የድጋፍ ሰልፍ በልዩ ልዩ ደማቅ ኩነቶች የታጀበና የአካባቢውን ባህላዊ እሴቶች ባንጸባረቀ መልኩ እየተከናወነ ይገኛል።

ሰልፈኞቹ በጋራ በመኾን በባህላዊ ውዝዋዜዎች፣ በልዩ ልዩ ዜማዎችና በስነ-ግጥሞች እንዲሁም ትርዒት በመታጀብ ሰልፉን ይበልጥ አድምቀውታል።

በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *