በብልፅግና ፓርቲ ዕሳቤ እምቅ የተፈጥሮ ፀጋዎች ወደ ሚጨበጥ ልማት ማሻገር ተችሏል – ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

Spread the love

በኮንታ ዞን፣ አመያ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ የይምረጡኝ ቅስቀሳ እና ህዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ በድምቀት ተካሂዷል።

በሰልፉ ላይ መልዕክት ያስተላለፋት ‎የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፣ በብልፅግና ፓርቲ ዕሳቤ እምቅ የተፈጥሮ ፀጋዎች ወደ ሚጨበጥ ልማት ማሻገር መቻሉን ተናግረዋል።

የብልፅግና ፓርቲ በሁሉም አከባቢዎች ፍትሀዊ የልማት ተደራሽነትን በማድረግ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ርዕሰ መስተዳድሩ፤

በዚህም የብልፅግና ፓርቲ ፍሬ የኾነው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እንዲሁም የኮንታ ዞን የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እያገኙ መምጣታቸውን አስገንዝበዋል።

ፓርቲ የህዝብ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ለመፍታት በሚያደረገው ያልተቋረጠ ጥረት የህዝብ የነቃ ተሳትፎ እንደነበረም ዶ/ር ነጋሽ ገልጸዋል።

የመጡ ለውጦች ተጠናክሮ እንዲቀጥሉና ቀጣይም ምላሽ ያላገኙ የህዝብ ጥያቄዎች እንዲፈቱ ህዝቡ ከመንግስት ጎን መቆም እንዳለበት የጠየቁት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የክልሉ መንግሥት ልማት በሁሉም አካባቢዎች ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ሰው ተኮር እሳቤዎችን በመተግበር በማህበራዊ ልማት ዘርፍ መጠነ ሰፊ ስኬቶችን ማስመዝገቡን ነው የክልሉ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን የገለጹት።

“በፓርቲ መሪነት የተገኙ ስኬቶቻችን ባስገኙልን የህዝብ ቅቡልነት ዕቅዶቻችን በተሻለ መልኩ ለማስቀጠል ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ የማግኘት ዕድል አገኝተናል” ያሉት አቶ ፍቅሬ በዚህም ባለፉት ዓመታት አስደናቂ ውጤቶችን አስመዝግበናል፡ ብለዋል።

የፖላቲካ ምህዳሩን በማስፋት የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታን በማጠናከር ለስርዓታዊ ልህቀት በር ተከፍቷል ያሉት አቶ ፍቅሬ፤ የዴሞክራሲ ባህል እንዲዳብር የፉክክርና የትብብር ሚዛን የጠበቀ የመነጋገርና መከራከር ባህል ለማዳበር እንደ ክልል ምቹ ምህዳር መፈጠሩን ገልጸዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ዘርፈብዙ ፈተናዎችን በድል በመሻገር አንጸባራቂ ድሎች እያስመዘገበ እንደሚገኝ የገለጹት የኮንታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታከለ ተስፉ አባል ደጋፊዎች በአደባባይ ላሳዩት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

በብልፅግና ፓርቲ ዕሳቤ ከልማት ወደኃላ የቀሩ አከባቢዎች ትኩረት አግኝተው እምቅ የልማት ፀጋዎች ተለይተው ወደ ልማት መግባታቸውን ነው አቶ ታከል ገልጸዋል።

በመጨረሻም ግንቦት 24 በሚከናወነው ጠቅላላ ምርጫ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ድምፅ በመስጠት እንደሀገር ሆነ በክልል ደረጃ እየመጡ ያሉ ልማቶች እንዲቀጥል እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

‎በዕድገቱ በዛብህ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *