በየአካባቢው ያለው የወርቅ ማዕድን ሀብት ለህዝብ በሚጠቅም መልኩ መሰራት ይገባል።ዶክተር ፍጹም አሰፋ

Spread the love

የፈዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን በክልሉ በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ እየተሰሩ ያሉትን የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝቷል፡፡

ቡድኑ በቤሮ ወረዳ በተለያዩ አካባቢ እየተሰሩ ያሉ የሌማት ትሩፋት፣ በጀባ ከተማ ተጨማሪ የትምህርትና የጤና ጣቢያ ግንባታ፣ የወርቅ አምራች ማህበራት የስራ እንቅስቃሴና ሌሎች የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በጉብኝ በቤሮ ወረዳ ጀባ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የተሰሩ የድሮንና የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ተጎብኝቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ የፌዴራል ሱፐርቪዥን ቡድን በቤሮ ወረዳው ከጀባ ከተማ ማህበረሰብና ከማዕድን አምራች ማህበራት ጋር በሠላም ፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ዙሪያም ተወያይተዋል ፡፡

የውይይቱ ተሳታፊዎች በወረዳ የፀጥታ፣ የመንገድና ሌሎች መሠረተ ልማት፣ የነዳጅ ዋጋ መናር እና ህገወጥ የወርቅ ግብይት እንዲሁም የወርቅ ዋጋ ማናስ አጠቃላይ ተግባራቸው ላይ ከፍተኛ ከፍተኛ ጫና እያስከተለ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በየጊዜው የምመረተው የወርቅ ምርት በሚፈለገው መጠን ጥቅም ላይ እንዲውልና ውጤት እንዲያመጣ የፀጥታ ሃይልን ማጠንከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የምዕራብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ጌታቸው ኬኒ የህዝብ ሀብት የሆነውን የወርቅ ማዕድን በተደራጀ መንገድ ቁጥጥር ለማድረግ ከህገወጥ መንገድ ለማስቀረት ህብረተሰቡ ጋር ተቀናጅተን የሚስተዋለውን ችግር የሚፈተ ሁኔታ እንደሚመቻች ገልጸዋል፡፡

የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ሚኒስተር ሚኒስቴር ዶክተር ፍጹም አሰፋ እንደሀገር የማዕድን ዘርፍ 5 ትኩረት ከሚሰጥባቸው የትኩረት መስኮች አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ሀብቱ በተለያዩ መንገድ በጥቂቶች እጅ በመውደቁ ህብረተሰቡ በሚፈለገው መጠን ሳይጠቀም ቆይቷል ብለዋል፡፡

በተለይም ቤሮ ወረዳ የወርቅ ማዕድን በጣም በሰፊ ያለበት ቢሆንም በዘርፉ ከሚታዩ ጫናዎች ምክንያት ህብረተሰቡ ያልተጠቀመበት መሆኑን አንስተዋል፡፡

በየአካባቢው ያለው የወርቅ ማዕድን ሀብት ለህዝብ በሚጠቅም መልኩ መሰራት ጥቅም ላይ እንዲውል እያንዳንዱ ማህበረሰብ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ ዶክተር ፍጹም አሰፋ አስታውቀዋል፡፡

ማዕድን ልማት የህብረተሰቡ መሸጋገሪያ እንጂ ዘላቂ ልማት አይደለም ያሉት ሚኒስትሯ ህብረተሰቡ ከወርቅ ማዕድን የሚገኘውን ሀብት ሌለ ልማት ማዋል አለበት ብለዋል ዶክተር ፍጹም አሰፋ፡፡

ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም አሰፋ በወረዳው ህብረተሰብን በማስተባበር ለህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ እየተሰሩ ያሉ የትምህርት እና ጤና ጣቢያ ግንባታ ስራ በጠም የሚደነቅ መሆኑን ጠቅሰው ይህ መልካም ተግባር ህብረተሰቡ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

በጉብኝቱ ፕላንና ልማት ሚኒስተር ሚኒስቴር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ጨምሮ ሌሎች ሚኒስቴር መስራያ ቤትና ተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም በቤሮ ወረዳ የጀባ ከተማው ማህበረሰብና ወርቅ አምራች ማህበራት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡

በተከተል ወ/ሚካኤል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *