ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በወጣትነት ዘመናቸው ሰላም አስከባሪ በመሆን ጭምር ሩዋንዳን ከችግር ለመታደግ አግዘዋል፡ – ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ

Spread the love

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በወጣትነት ዘመናቸው ሰላም አስከባሪ በመሆን ጭምር ሩዋንዳን ከችግር ለመታደግ አግዘዋል ሲሉ የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሩዋንዳውያን የ”ኪዊቡካ 30″ ዓመት መታሰቢያ መርሐ ግብር ላይ ታድመዋል፡፡

መርሃ ግብሩ በሩዋንዳ የተፈጸመውን የዘር ጭፍጨፋ 30ኛ ዓመት የሚያስብ ነው፡፡

በመርሃ ግበሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሚ ሩዋንዳን በወቅቱ ከገጠማት ችግር ለመታደግ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት እገዛ አድርገዋል ነው ያሉት፡፡

በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ መንግስትን ያመሰገኑ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በወጣትነት ዘመናቸው ሰላም አስከባሪ በመሆን ጭምር ሩዋንዳን ከችግር ለመታደግ አግዘዋል በማለት ተናግረዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *