እስካሁን የተደረጉ የባህል ስፖርቶችና ባህል ፌስቲቫል ውድድሮች ውጤት ተገለጸ::

Spread the love

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ በሸካ ዞን ማሻ ከተማ የሚካሄደው 21ኛው የባህል ስፖርቶች ውድድርና 17ኛው የባህል ፌስቲቫል ውድድር ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።

ሁለተኛ ቀኑን በያዘው ባህል ስፖርቶች ውድድርና ባህል ፌስትቫል ቡብ፥ ገበጣ 12 ጉድጓድ የወንዶችና የሴቶች፣ሻህ የወንዶችና የሴቶች፣ ኮርቦ የሴቶች ፍፃሜ እና ሌሎች ባህላዊ የስፖርት ውድድሮችና ባህል ፌስቲቫሎች በሁለቱም ፆታዎች ተካሂደዋል።

በዚህም ኩርቦ የሴቶች ፍፃሜ ውድድር 1ኛ ሸካ ዞን ፣ 2ኛ ኮንታ ዞን እንዲሁም ካፋ ዞን 3ኛ በሆነ ውጤት መቋጫውን አገኝተዋል።

በቡብ ውድድር ወንዶች ሸካ ዞን ዳውሮ ዞንን 2ለ1፣ ካፋ ዞን ኮንታ ዞንን 2ለ1፤ ቡብ በሴቶች ሸካ ዞን ኮንታ ዞንን 2ለ0 ፣ዳውሮ ዞን ካፋ ዞንን 2ለ1 ያሸነፉ ሲሆን በገበጣ ባለ12 ጉድጓድ ወንዶች ካፋ ዞን ኮንታ ዞንን 2ለ0 እና ሲያሸንፍ ሸካ ዞን ከዳውሮ ዞን ጋር ባደረገው ግጥሚያ 2ለ0 ማሸነፍ ችሏል።

በገበጣ ውድድር ባለ12 ጉድጓድ ሴቶች ሸካ ካፋን 2ለ1 እና ምዕራብ ኦሞ ኮንታን 2ለ0 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

በሻህ ወንዶች ውድድር ካፋ ሸካን 2ለ0 ፣ዳውሮ ኮንታን 2ለ0 ያሸነፉ ሲሆን የሻህ ውድድር በሴቶች ዳውሮ ሸካን 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸውን ከባህል ስፖርቶችና ባህል ፌስቲቫል ፌደሬሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል።

በፍቅር ከበደ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *