በረመዳን ጾም ወቅት የታየው የመረዳዳትና የመደጋገፍ መልካም ተሞክሮ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ሕዝቦች ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት አሳሰበ፡፡asxds

Spread the love

ለ1 ሺህ 4 መቶ 45ኛ ጊዜ ለሚከበረዉን የዒድአልፈጥር በዓል መሰረት የሆነዉ የረመዳን ወር ጾምና ጸሎት በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች በሰላማዊ ሁኔታ እየተከናወነ ስለመሆኑም ተገልጿል፡፡

ከአምስቱ የእስልምና እምነት መሠረቶች ዉስጥ አንዱ እንደሆነ የሚታመነዉ የረመዳን ወር በመላዉ አለም በሚገኙ የእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበር በዓል መሆኑን የገለጹት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮዽያ ሕዝቦች ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼህ መሀመድ ጅብሪል ናቸው።

በጸም ወቅት የሚከናወኑ መንፈሳዊ ተግባራትን በግልና በጋራ በማከናወን የዘንድሮው የረመዳን ወር ጾም በሰላማዊ ሁኔታ እየተከበረ ነው ብለዋል ፡፡

ረመዳን ከእስላማዊ የእምነት ግዴታዎች አንጻር መደጋገፍና መተባበርን አጥብቆ ያስተምራል ያሉት የደቡብ ምዕራብ እትዮዽያ ሕዝቦች ክልል እስልምና ጉዳይ ምክር ቤት የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሸረፈዲን ኑሩ ይህን የፈጣሪ ትዕዛዝ ባለማጓደልና ያለንን በማካፈል የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል በማለት ምክራቸውን ለግሰዋል፡፡

በረመዳን ወር ጾም ዉስጥ ዱኣ፣ ዘካና ሰደቃ ትልቅ ቦታ የሚሰጣቸውና በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ በክብር የሚደረጉ ተግባራት ናቸው ያሉት አቶ ሸረፈድን ለሀገርና ለህዝብ ሰላም መጸለይም ደግሞ ሁሌም የሚዘወተር ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊትም በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ እንደተለመደው በዘንድሮዉ የረመዳን ወር ጾም ወቅት ከሁሉ የእምነቱ ተከታዮች የተሰበሰበ ዘካ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ መደረጉን የተናገሩት የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አባል አቶ አብዱረዛቅ ሣህሌ ይህም ትልቅ ሰብዓዊ ተግባር ነው ብለዋል፡፡

በአጠቃላይ የተሰበሰበው ከ1 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ብር የተዘጋጀው ዘካ ለበዓል መዋያ ከ9 መቶ በላይ ለሚሆኑ አቅመ-ደካማ አባ-ወራዎች በአቅራቢያቸው ባሉ መስጂዶች በኩል እንዲደርሳቸው መመቻቸቱንም አቶ አብዱረዛቅ ተናግረዋል።

መጠያየቅ፣ መደጋገፍና መዋደድ በቅርብ ካለዉ ጎረቤት ጀምሮ እስከ ሀገር ከዛም ለዓለም መድረስ ለእስልምና እምነት ተከታዮች የተሰጠ ሀላፊነት ነው ያሉት ወ/ሮ ዘምዘም ኑሩ ካነጋገርናቸው የእምነቱ ተከታዮች መካከል ናቸው።

ይህንን ሃይማኖታዊ ግዴታ ሁሉም በትጋትና በእምነት ሊፈጽም እንደሚገባ የተናገሩት ወ/ሮ ዘምዘም ለአለም እዝነት ለሰው ልጅ ሁሉ ርህራሄና ፍቅርን ማሳየት ሀይማኖታዊ ግዴታ በመሆኑ አንዳችን ለአንዳችን ልንደርስና ልንደጋገፍ ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል ሲል ደ.ሬ.ቴ.ድ ቦንጋ ቅርንጫፍ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *