
ከለውጡ ወዲህ የህዝቡ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በቅርበት ለመፈታት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል ሲሉ የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን ገለጸ።
የሚዛን አማን አየር ማረፊያ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
የቤንች ሸኮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀብታሙ ካፍቲን ለኢፕድ እንደገለጹት፣ ዞኑ በግብርናው፣ በማእድን፣ በቡናና በቅመማቅመም ሀብት የታወቀ በመሆኑ ክልሉ የኢኮኖሚ የስበት ማእከል ነው። ይህን በዘላቂነት ለመስራት የአካባቢውን ሰላም በዘላቂነት ማረጋገጥ ወሳኝ ነው።
በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚና በአስተዳደር ዘርፍ ያሉ ቅንጅታዊ አሰራሮችን ለማስቀጠል ሰላም ወሳኝ ስለሆነ በዞኑ ያለውን ሰላም ማረጋገጥ ቁልፍ ስራ አድርጐ ሲሰራ ቆይቷል። ይህን በማከናወን ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው።
ዞኑ በአመት ከ30 ሺ ቶን በላይ ቡና ለማእከላዊ ገቢያ የሚያቀርብ መሆኑን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው፣ ከቡና እና ቅመማቅመም ልማት በተጨማሪ በሰብሎች ልማት 90 ሺ ሄክታር መሬት እየለማ ነው።
በቡናው ዘርፍ ያለው የግብይት ትስስር ችግር በመኖሩ በዞኑ ያሉ ቡና ነጋዴዎችና አርሶአደሮች ከፍተኛ ቅሬታ እያስነሳ ነው። ችግሩን የሚመለከታቸው አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊፈቱ እንደሚገባ አስተዳዳሪው ገልጸዋል።
እንዴኢፕድ ዞኑ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ከባቢ ነው። በተለይ ከአዲስ አበባ ሩቅ በመሆኑ ባለሀብቶች መጥተው እንዲያለሙ እንቅፋት ነበር ያሉት ዎና አስተዳዳሪው አሁን ላይ የሚዛን አማን አየር ማረፊያ ግንባታ ሲጠናቀቅ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። የሰላምና የጸጥታ ሁኔታው ለኢንቨስትመንት ምቹ መሆኑን ጠቁመዋል።
