የኢትዮጵያ ፈተናዎችን ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)::

Spread the love

የኢትዮጵያ በፈተናዎች ሁሉ የተሻገረ ያለመበገር ፅናት የምጣኔ ሀብት መረጋጋትንና ምርታማነትን ባስቀደሙት በመዋቅራዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ስራዎቿ ማሳያነት ይገለጣል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ተናገሩ።

በብሔራዊ የምክክር ኮሚሽን በሚመራው ስራ ምክክር እና እርቅ የሰላም ፍላጎታችን እና ተምኔታችን ማጠንጠኛ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል።

ትምህርትን ተደራሽ በማድረግ ብሎም ወጣቶችን በማብቃት ኢትዮጵያ ሁለት ሚሊዮን አዳዲስ ስራዎችን ለመፍጠር እንዳለመችም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ገልጸዋል።

አረንጓዴ ዓሻራ በመሰሉ ንቅናቄዎች ኃይል ለሁሉም ማዳረስ፣ የዲጂታል ሽግግር እና የተፈጥሮ ከባቢን የመንከባከብ ተግባራትን ለመከወንም ትኩረት ትሰጣለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር ለአሀጉሩ ድጋፉን እንዲያጠናክር ጥሪ ታደርጋለች ማለታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ ትስስር ገፅ የተገኘው መረጃ ያመለክታል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *