በአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ከ50 ሺ በላይ ለሚሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ስልጠና ይሰጣል- ትምህርት ሚኒስቴር::

Spread the love

በዘንድሮው ዓመት በአጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የመምህራን የክረምት ስልጠና ከ50 ሺ በላይ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ስልጠና እንደሚሠጣቸው ተገለፀ።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት ስልጠናው አሁን እያስተማሩ ያሉ መምህራን በሚያስተምሩት የትምህርት ይዘትና የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ላይ ክህሎት እንዲይዙ ያለመ ነው።

መምህራኑ በሚያገኙት ስልጠና በሚያስተምሩት ትምህርት ላይ በበቂ ሁኔታ ማስተማር የሚያስችላቸውን ክህሎት እንደሚያገኙ መግለጻቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ በበኩላቸው የመምህራንና ትምህርት አመራሮች የክረምት ስልጠና የተሳካ እንዲሆን ክልሎች ተባብረው መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

የመምህራን የክረምት ስልጠና አተገባበር ስትራቴጂ በመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በውይይቱም የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ለመምህራን የሚሰጠው ስልጠና መምህራኑ በሚያስተምሩት ትምህርት ይዘትና የማስተማሪያ ስነ ዘዴ ላይ በመሆኑ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ጠቃሚ መሆኑንም አንስተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *