ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታና የንቅናቄ ስራዎቻችንን አጠናክሮ በማስቀጠል ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በተናበበ መልኩ መሰራት ይገባል፦ አቶ ነጋ አበራ::

Spread the love

ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታና የንቅናቄ ስራዎቻንን አጠናክሮ በማስቀጠል ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በተናበበ መልኩ መሰራት ይገባል ሲሉ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አቶ ነጋ አበራ ገለጹ።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2016 ዓ.ም የዘጠኝ ወራት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የቀጣይ ወራት የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ አካሂዷል።

በመድረኩ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ነጋ አበራ እንዳሉት የውስጠ ፓርቲ አንድነትን በማጠናከርና ያሉትን ተግዳሮቶችን በትበብር እና በአንድነት መንፈስ ለመፍታት መስራት ይኖርብናል ብለዋል።

የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል እንደ ሀገር በፖለቲካ ምህዳሩ የብልጽግና እሳቤዎቻችን የበላይነት እንዲያገኙ ለማስቻል አመራሩ ከወዲሁ ሰፊ ስራ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ጠንካራና ተግባቦት ላይ የተመሠረተ የፖለቲካ ስራዎችን በመስራት የፓርቲውን እሳቤዎች በህብረተሰቡ ዘንድ ማስረጽ ይኖርብናል ነው ያሉት።

የውሰጠ ፓርቲ ዲሞክራሲን ለማረጋገጥና ግልጸኝነትን በተላበሰ አኳኃን መስራት ይገባል ያሉት አቶ ነጋ በፖለቲካና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ የህዝብን አብሮነት የሚያጎለብቱ ተግባራት ላይ በትኩረት እንደሚሰራ አስገንዝበዋል ።

የንቅናቄ ስራዎችን በበላይነት በመምራት እና ውጤት ተኮር መሆን ይኖርብናል ያሉት አቶ ነጋ በዚህም በጊዜ የለንም መንፈስ ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ ለቀጣይ በጀት ዓመት ከወዲሁ መዘጋጀት ያስፈልጋል ብለዋል።

ዘላቂነት ያለው ሰላምን ለማረጋገጥ አመራሩ አጽንኦት ሰጥቶ መስራት እንዳለበት የገለጹ ሲሆን ገዥ ትርክትን ለማጽናትና ወደ ህዝቡ የማስረጽ ተግባር በተጠናከረ መንገድ መስራት ከሁሉም አመራርና አባል ይጠበቃል ብለዋል።

ጠንካራ አደረጃጀቶቻችንን በመፍጠር የተጀመሩ የልማት ግቦችን ከዳር ለማድረስ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ጠቅሰው የነበሩ ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል እና ክፍተቶችን በመሙላት ከወዲሁ ርብርብ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ አለሙ ገብሬ እንደገለጹት ዘርፉ ባለፋት ዓመታት የአመራሩና የአባሉን የፖለቲካ አቅም በመገንባት ረገድ ጥሩ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይ አደረጃጀቶች ይበልጥ አጎልብቶ በመጠቀም የህዝቡን አቅም አስተባብሮ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት አለብን ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የውይይት መድረኩ የተግባራት አፈጻጸምን በመፈተሽ ጥንካሬዎችን ለማስቀጠል እና ጉድለቶችን ፈጥኖ ለማረም ለቀጣይ ስራዎች ምቹ ሁኔታን የፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል።

በመድረኩ አንዱ ከእንዱ ልምድ የተወሰደበት እና በሚስተዋሉ ክፍተቶች ላይ በጋራ ማስተካከል እንደሚገባ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *