
በኢኮኖሚ ጉዳዮች
🔴 ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋ በዓለም አቀፍ በተከታታይ በሚያደርሱብን ቀውስ ውስጥ ነው ያለነው፤
🔴 በቅርብና በሩቅ ያለው ቀውስ ወደ እኛ ሲመጣ የኢኮኖሚ ጉዞውን አተካች አድርጎብናል፤
🔴 የለውጡ መንግስት በተለየ የገጠሙን ተግዳሮቶች ነበሩ፤ አንደኛው የወረስነው እዳ ነው፤
🔴 መሮጥ በሚገባን ልክ ለመሮጥ ፈተና የጋረጠብን ቢሆንም፤ ከፈተናዎች ውስጥ እድልን ፈልቅቆ የማውጣት በተቀየረ የአሰራርና የስራ ባህል መከተል በመቻላችን እጅግ ስኬታማ አመት ነወ ያሳለፍነው፤
🔴 በዚህ አመት በሁሉም ዘርፍ በስኬት ነው ያሳለፍነው፤
🔴ኢትዮጵያ ውስጥ 64 ሺህ ሰዎች የሚከፍሉት ግብር ኢትዮጵያ ለምታስበው ልማት ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት እንቸገራለን፤
🔴 ላለፉት ስድስት አመታት አንድ ዶላር ኮሜርሻል ብድር አልወሰድንም፤
🔴 ኢትዮጵያ ያለበት ዓለም አቀፍ ብድር ወደ 17 ነጥብ 5 ከጂዲፕው ዝቅ ብሏል፤
🔴 ዘንድሮ ከአምና 4 በመቶ የበለጠ የውጭ ንግድ ገቢ ተገኝቷል፤
🔴 አሁንም ኢትዮጵያ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ ናት፤
🔴 ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆኑ ምርቶችን በአገር ውስጥ ምርት መተካት ችለናል፤
🔴የፋብሪካ ምርቶችን 40 በመቶ በአገር ውስጥ ምርት መተካት ችለናል፤
🔴ለነዳጅ አራት ቢሊዮን ፣ ለማዳበሪያ አንድ ቢሊየን እንዲሁም ለእዳ ክፍያ 2 ቢሊዮን ዶላር በአመት እናወጣለን
🔴 ከለውጡ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ መኪና በእጥፍ አድጓል፤ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የግል መኪናዎች ናቸው፤
🔴 የፋይናንስ ዘርፉ ባንኮች ዛሬ ከ17 ወደ 32 ደርሰዋል፤ ቅርንጫፎቻቸውም አድጓል፤
🔴 38 ሚሊዮን የነበረው የቁጠባ ደብተር ከ100 ሚሊዮን በልጧል፤
🔴 የፋይናንሻል ዘርፉ ጤናማና መሻሻል ያሳየ ነው፤ ባንኮች ትርፋማም ናቸው፤
ዛሬ 47 ሚሊዮን ዜጎች በሞባይል ባንኪንግ ይጠቀማሉ፤
🔴 እዚህ የደረስነው ኢትዮ ቴሌኮም ለዘመናት ተኝቶ ከነበረበት ሳፋሪኮም ሊመጣ ነው ሲባል ነቅቶ ነው፤
🔴 ይሄንን ስኬት በባንኮች መድገም እንፈልጋለን፤
🔴 ለረጅም ጊዜ ዘግተን አቆይተናቸዋል፤ አሁን እንደዛ አንቀጥልም፤
🔴 የዋጋ ግሽበት ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሁሉ ዓለም አጀንዳ ሆኗል፤
🔴 በዓለም ላይ ባሉ አገራት በሚካሄዱ ምርጫዎች ዋናው የመከራከሪያ ጉዳይ ይሄው የኑሮ ውድነት ሆኗል፤
🔴 ስንዴ ባለፈው አመት 395 ሚሊዮን ነበር ያመረትነው፤ ዘንድሮ 587 ሚሊዮን ኩንታል ነው ያመረትነው፤
🔴 ከዚህ በላይ ምርት የማሳደግ አቅምና እድል አለን፤
🔴 ከለውጡ በኋላ ዘመናዊ ቀፎ ቁጥር 1 ሚሊዮን ደርሷል፤ የማር ምርት ከሰባት እጥፍ በላይ አድጓል፤
🔴 ምግብ ነክ ለሆኑ ከውጭ የገቡ ምርቶች መንግስት ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር እፎይታ ሰጥቷል፤
🔴 የኢትዮጵያ የዋጋ ግሽበት ወደ 23 በመቶ ዝቅ ብሏል፤
🔴 ዘንድሮ 24 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት ለማረስ እቅድ ተይዟል፤
🔴 ዘንድሮ አንድ የተሳካልን መስክ ቢኖር የኢንዱስትሪው ዘርፍ ነው፤ ይሄ የሆነው ኢትዮጵያ ታምርት በሚለው ንቅናቄ ነው፤
🔴 ዘንድሮ በነባር የሲሚንቶ ፋብሪካ ብቻ 30 በመቶ የምርት እድገት መጥቷል፣
🔴 ለሚ በቅርቡ ስራ ይጀምሯል፤ ይሄ ፋብሪካ አሁን እንደ አገር የሚመረተወን ምርት 50 በመቶ ያህል ብቻውን ያመርታል፤
🔴 በተለይ የሌማት ትሩፋት የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ይገኛል፣
🔴 መንግስት 10 ቢሊዮን ብር ገቢ በመተው መሰረታዊ ሸቀጦችን ከቀረጥ ነጻ እንዲገባ አድርጓል፣
