በኮንታ ዞን በ50 ሄክታር ማሳ ላይ የመስራች ዘር ብዜት ሥራ እየተከናወነ ነው።

Spread the love

በክልሉ ግብርና ቢሮና የምርምር ኢንስቲትዩት አስተባባሪነት በኮንታ ዞን ‘የመስራች ዘር’ ብዜት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው በተገኙበት ተጀምሯል።

በክልሉ ምርምር ኢኒስቲትዩት የታርጫ ምርምር ማዕከል በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ሼታ ቀበሌ በ50 ሄክታር መሬት ላይ የስንዴና ባቄላ ዘር ብዜት የክልል፣ የዞንና የወረዳው አመራሮችና የአከባቢው ነዋሪዎች በተገኙበት በይፋ ተበስሯል።

የተዘራው ‘መስራች ዘር’ በቀጣይ ለማባዛት የሚዘጋጅ እንደሆነ የተገለጹት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ማስረሻ በላቸው አርሶአደሮች የምርጥር ዘር ምርቱ ሲደርስ ለምርምር ኢንስቲትዩት ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ተነግረዋል።

ከአከባቢው ስነ ምህዳር ጋር ተስማሚ የምርጥ ዘር ለአርሶአደሮች እንዲቀርብ ለማስቻል የክልሉ መንግሥት ለምርምር ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ትኩረት መሰጠቱን አቶ ማስረሻ ጨምረው ገልጸዋል።

ምርምር ማዕከሉ የተሻሻሉ ዘሮችን ለማቅረብ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኘ የገለጹት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አማኑኤል ዓለሙ የሚለማው የመስራች ዘር በቀጣይ ለዘር ብዜት ዓላማ የሚውል በመሆኑ አስረድተዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለው የምርጥ ዘር እጥረትን ለመቅረፍ የክልሉ መንግሥት በ75 ሄክታር መሬት ላይ የምርጥ ዘር ብዜት እያከናወነ መሆኑ አብራርተዋል።

በዞኑ በ2015/16 መኸር እርሻ ወቅት 18,844ሄ/ር መሬት በቴክኖሎጅና በመደበኛ በተለያዩ ሰብል አይነት ለማልማት ከታቀደው ውስጥ 1,745ሄ/ር መሬት በኩታ ገጠም እንደሚለማም በመድረኩ ተገልጿል።

ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የተሻሻለ ዘር ለአርሶአደሮች የማቅረብ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ያሳሰቡት የዞኑ ዋና አስተዳደር አቶ ነጋ አበራ የክልሉ ግብር ቢሮ ከምርምር ኢንስቲትዩት ጋር በመቀናጀት በዞኑ አመያ ዙሪያ ወረዳ የተጀመረው የመስራች ዘር ብዜት ስራ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *